ማዕድ ማጋራት የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች 200ሺህ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸውና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።
ማዕድ ማጋራት ለነዋሪዎቻችን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን የምንገልፅበት እዲሁም እርስ በርስ መተሳሰብን የምናዳብርበት የሰው ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ከንቲባዋ አክለውም እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ዛሬም መስጠት አያጎድልም ብለው ከጎናችን የቆሙ የከተማችን ባለሃብቶችን፣ ተቋማትንና ወጣት በጐ ፍቃደኞችን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ ብለዋል።
ምላሽ ይስጡ