ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እ.ኤ.አ 2024 በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የስደተኞች አደጋ፣ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ እንዲሁም የታጣቂዎች ግጭት ከፍተኛ ቀውስ ያስከተለበት ጊዜ እንደነበር የአናዶሉ ዘገባ ገልጿል፡፡
ቀውሶቹም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ላይ ተጽዕኖ ፈጥረዋል ተብሏል፡፡
ትናንት የተጠናቀቀው 2024 አፍሪካ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ገጥሟት ያለፈ ጊዜ እንደነበር ነው የተመላከተው፡፡
በአመቱ የሙቀት መጠን መጨመር፣ ድርቅ እና ጎርፍ በተለያዩ ሀገራት ጉዳት አስከትሏል፤ በርካቶችም በዚሁ ምክንያት ተፈናቅለዋል። ለአብነት በመስከረም ወር በናይጄሪያ በጎርፍ መጥለቅለቅ እና በግድብ መደርመስ አደጋ 1 ሚሊዮን ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው፤ በትንሹም የ37 ሰዎች ህይወት ማለፉን ዘገባው ጠቅሷል፡፡
በሶማሊያም 6 ነጥብ 9 ሚሊዮን ወይም ከ5 ሶማሊያውያን 2ቱ በከፋ ድርቅ ሳቢያ ሰብዓዊ ርዳታ ጠባቂ እንደነበሩ ያመላከተው ሪፖርቱ፤ ሀገሪቱ በ2024 ከአለም አንደኛዋ የተራበች አገር ነበረች ብሏል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ስደተኞች ከግጭት ለመሸሽ እና የተሻለ ህይወት ፍለጋ ባህር ሲያቋርጡ ህይወታቸው እንዳለፈም ተመላክቷል፡፡
እ.ኤ.አ. ከ2024 መጀመሪያ ጀምሮ በአፍሪካ ከ1ሺ 300 በላይ ዜጎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተዘግቧል።
ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኮንጎ፣ ማሊ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ግጭቶች እንደነበሩ አስታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ