ሕዳር 11 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው የንጉሥ አብዱላህ የፋይናንስ ዲስትሪክት ውስጥ የሚገኘው የሀገሪቱ የሕዝብ ኢንቨስትመንት ፈንድ (PIF) ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ትናንት ኅዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም በደረሰ የሚሳኤል ጥቃት ጉዳት እንደደረሰበት ተገለጸ።
በየመን የሁቲ ታጣቂዎች ወደ ሪያድ የተተኮሰውን ሚሳኤል ለመመከት በተወሰደ እርምጃ ሳቢያ በወደቀ ፍርስራሽ በሕንፃው የተወሰኑ ፎቆች እና በአቅራቢያው በሚገኙ ሕንፃዎች ላይ ቁሳዊ ጉዳት መድረሱን የሳዑዲ ሲቪል መከላከያና የሀገሪቱ የዜና ወኪል (SPA) አረጋግጠዋል። ሆኖም በጥቃቱ ምክንያት በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ታውቋል።
ክስተቱን ተከትሎ የፋይናንስ ዲስትሪክቱ መግቢያዎች በሙሉ ተዘግተው ሰዎች ከአካባቢው እንዲወጡ ሲደረግ፣ አምቡላንሶችና የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች በስፍራው መሰማራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። በሪያድ ረጅሙን ሕንፃ የሚያቅፈው ይህ የንጉሥ አብዱላህ የፋይናንስ ዲስትሪክት ጥቃት ሲደርስበት በዚህ ወር ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ከቀናት በፊትም በሁቲዎች ጥቃት በሳዑዲ አራምኮ ሕንፃ ላይ ተመሳሳይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
ይህ ፍንዳታ በሪያድ የተሰማው የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን ከአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) አዛዥ አድሚራል ብራድ ኩፐር ጋር በወታደራዊ ግንኙነትና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተወያዩ ከጥቂት ጊዜ በኋላ መሆኑም ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ፊንላንድ የሐሰት ዜናን መለየትን ከ6 ዓመት ጀምሮ ማስተማር ጀመረች
👉በትምህርት ስርዓቱ አካታለች ነው የተባለው።
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰፊው የሐሰት መረጃ መስፋፋት በፈጠረው የዲጂታል ዘመን፣ ፊንላንድ የሐሰት መረጃዎችንና... read more
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተጨመረለት የ1 ዓመት የስራ ቆይታ አጀንዳዎችን የመቅረፅ እና ይፋ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ገለጸ
ሰሞኑን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ... read more
ቀጠናዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ዘገባዎች ሲሰሩ የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም መሰረት በማድረግ መሆን እንዳለበት ባለሙያዎች ገለጹ
በውጭ ቋንቋዎችም ሆነ በሀገር ውስጥ ቋንቋ የሚሰሩ ዘገባዎች የሀገርን ብሄራዊ ጥቅም ባከበረ መልኩ መሆን እንደሚገባው የሚዲያና የጥናት ተቋማት ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
በዓሉ ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲጠናቀቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎችን እንዲደረግ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል
👉 የበዓል ስራዎቸን በሚከናወኑበት ጊዜ ሁሉንም ስራዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከማከናወን መቆጠብና ስራዎችን በቅድመ ተከተል እንዲሁም እንደቤተሰብ አባል ብዛትና ችሎታ ስራን... read more
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ለስፔስ ኤክስ (SpaceX) መስራች ኢሎን መስክ ከፍተኛ የመንግሥት የክብር ሜዳሊያ አበረከቱ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ የስፔስ ኤክስ (SpaceX) ባለቤት ለሆኑት ኢሎን መስክ የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ... read more
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይኖሩ የነበሩ የህግ ታራሚዎች ገላን አካባቢ ወደ ተገነባው አዲስ ማረሚያ ቤት ሊዘዋወሩ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደተገነባው ገላን... read more
በአማራ ክልል ሁለት ሰዎች ላይ የኤም ፖክስ (Mpox) ቫይረስ መገኘቱ ተገለጸ
በአማራ ክልል ኤም ፖክስ (MPox) ተላላፊ ቫይረስ በሽታ በመተማ እና ባሕርዳር ከተሞች በሁለት ሰዎች ናሙና ተወስዶ መረጋገጡን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ... read more
ብሉቱዝ ለሃከሮች አዲስ የጥቃት መስመር ሆኖ ተገኘ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዘመናችን ለተለያዩ መሳሪያዎች መተሳሰሪያነት በስፋት የምንጠቀምበት የብሉቱዝ ቴክኖሎጂ ለሳይበር ወንጀለኞች አዲስ የጥቃት መስመር ሆኖ እየተገኘ... read more
ሱዳን ለ30 ወራት ተዘግቶ የቆየውን የካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ልትከፍት ነው
ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፈው ሚያዚያ 2023 በአገሪቱ የጦር ኃይል እና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ጊዜ በኋላ... read more
በተመረጡ ስድስት ዘርፎች 5ኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና መርሃ-ግብር ሊካሄድ ነዉ
በተመረጡ 6 ዘርፎች ላይ 5ኛው የጣፋጭ ህይወት የምስጋና መርሃ-ግብር ሊካሄድ መሆኑን ጣፋጭ ህይወት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በየአመቱ እየተከናወነ ያለዉ... read more
ምላሽ ይስጡ