መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመጪው መስከረም 16 ቀን 2019 የሚከበረው የደመራ እንዲሁም የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ቢሮው የሰላምና ፀጥታ ሥራውን እየሠራ እንደሚገኝ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሥሐ ጥበቡ፤ በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር የፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አስቀድሞ ከማህበረሰቡ ጋር በቂ ውይይት መደረጉን የተናገሩት አቶ ፍሥሐ፤ የኢትዮጵያን ገጽታ ሊገነባ በሚችል ደረጃ በዓሉ እንዲከበር ከፀጥታ አኳያ ተገቢው ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል። ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የሃይማኖት አባቶች በሚያስቀምጡት ሥርዓት መሠረት በዓሉ እንዲከበር ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አሳስበዋል። ከፀጥታ ጎን ለጎን በየሰፈሩ በሚካሄደው የደመራ ማብራት ሥርዓት ላይ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይከሰት ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በዚህ በዓል ላይ በርካታ የሀገር ውስጥ እንዲሁም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ቱሪስቶች የሚገኙ በመሆኑ፣ የፀጥታ አካላት አስቀድመው ሕግና ሥርዓትን በጠበቀ መልኩ የፍተሻ እና የቅኝት ሥራዎችን እንደሚያደርጉ አመላክተዋል። መስቀል እንዲሁም በቀጣይ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ቻይናውያን ሳይንቲስቶች በሰው ሰራሽ ማህፀን አማካኝነት ህጻናትን የሚወልድ የመጀመሪያውን “ሮቦት” እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ
ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቻይና ሳይንቲስቶች በዓለም የመጀመሪያ የሆነውንና ፅንስን በሰው ሰራሽ ማህፀን ውስጥ ተሸክሞ በሰላም መገላገል የሚችል የእርግዝና ሮቦት... read more
በቴሌግራም የተደራጀ የወሲብ ወንጀል መሪ በደቡብ ኮሪያ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በደቡብ ኮሪያ፣ በታዋቂው የቴሌግራም መተግበሪያ ላይ የጾታ ወንጀል ድርጊቶችን ሲያደራጅ የነበረው የወንጀል ቡድን መሪ የዕድሜ ልክ... read more
በአማራ ክልል የተመረተ ከ20 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ኦፓል ለውጭ ገበያ አቅርበናል👉የክልሉ የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ
በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመረተ ከ20 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የኦፓል ማዕድን በማዕከላዊ ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ መቅረቡን የክልሉ... read more
የስነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 92 አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በ2017 በጀት ዓመት 12 ወራት ተቋሙ ተግባራዊ ባደረገው ዲጂታል የሙስና ተግባር መጠቆሚያ ሞባይል አፕሊኬሽን... read more
ኢትዮጵያ በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የመጀመሪያውን የቤት መግዣ ብድር ማጠናከሪያ ኩባንያ ልታቋቁም ነው
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) በሀገሪቱ የመጀመሪያው የሆነውን የቤት መግዣ ብድር... read more
ግዙፍ የሆኑ የከተማዋ ሞሎች እና ሪል-ስቴቶች የአከራይ ተከራይ ግብር እየከፈሉ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ
ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግዙፍ ህንጻ የሚያከራዩ እና ሪል-ስቴት ባለቤቶች የአከራይ ተከራይ ግብር እንዲከፍሉ... read more
የዓለም ረጅሙን የሥራ ዘመን ያስመዘገቡት የ100 ዓመቱ አዛውንት ክብረ ወሰን ሰበሩ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዋልተር ኦርትማን የተባሉ ብራዚላዊ አዛውንት በአንድ ኩባንያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በመሥራት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት... read more
ቴሌግራም የተጠቃሚዎችን ደኅንነት በተመለከተ የአቋም ለውጥ አደረገ
ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተጠቃሚያቸው እያደገ ከሚገኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መተግበሪያዎች መካከል አንዱ የሆነው ቴሌግራም ሲወቀስበት የነበረውን የተጠቃሚዎች ደኅንነት... read more
🚀 የኢሎን ማስክ አስደንጋጭ ትንበያ፡ «እ.ኤ.አ. በ2036 ገንዘብ ዋጋ የሌለው ባዶ ወረቀት ሊሆን ይችላል!»
ሐምሌ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ፈጥነት ማደጋቸውን ከቀጠሉ፣ እ.ኤ.አ. በ2036 በዓለማችን ላይ... read more
ምላሽ ይስጡ