መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገሪቱ ከሚገኙ አካል ጉዳተኞች መካከል 11.8 በመቶ ያህሉ ብቻ የትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማኅበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብሬ ተሾመ ተናግረዋል። የትምህርት ዕድል ያላገኙ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነና ሽፋኑ አሁንም ዝቅተኛ መሆኑን ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩም ገልጸዋል። ወላጆች አካል ጉዳተኛ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ ከመላክ አንጻር ክፍተት እንዳለባቸው የተናገሩት ኃላፊው፤ ወላጆች ይህንን ችግራቸውን በመቅረፍ ልጆቻቸውን የማስተማር ቀዳሚ ኃላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም ብለዋል። የትምህርት ዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም በሚያካሂዱት የቅኝትና የቁጥጥር ሥራ ወቅት፤ በየአካባቢው ካሉ አካል ጉዳተኞች ምን ያህሉ ትምህርት ቤት እንደገቡ ሊከታተሉና አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአማራ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ያሳተማቸውን የብሬል መጻሕፍት ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ተደራሽ ቢያደርግም በቂ እንዳልሆነ የሚናገሩት አቶ ገብሬ፤ የማኅበሩ ግዴታ መንግሥት ይህንን እንዲያሟላ መጠየቅ ቢሆንም፣ አንዳንድ የመንግሥት አካላት ሳይቀሩ ማኅበሩ እንዲያሟላ ሲጠይቁ ይስተዋላል ብለዋል። የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት ግብዓቶችን በሚፈለገው ልክ ማቅረብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የአካል ጉዳተኞችና የመምህራን ማኅበራትን ጨምሮ ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት፣ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ዜጋ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመጣው ከቡናማ ላሞች ነው ብለው ያምናሉ ተባለ
ሐምሌ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)23 ሚሊዮን አሜሪካውያን የቸኮሌት ወተት የሚመነጨው ከቡናማ ቀለም ካላቸው ላሞች ነው ብለው እንደሚያምኑ ተገለጸ። ይህ መረጃ... read more
በአዲስ አበባ ከተማ እየተስተዋለ ያለዉ የነዳጅ እጥረት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚፈታ ተገለጸ
ባለፉት ቀናት በመዲናዋ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የነዳጅ እጥረት በማጋጠሙ ረጃጅም ሰልፎች በየማደያዎች ተስተዉሏል።
ይህንን መነሻ በማድረግ መናኸሪያ ሬድዮ የአዲስ አበባ ንግድ... read more
በኢትዮጵያ በዘንድሮ አመት 270 ሚሊየን ኮንዶም እንደሚያስፈል ተገለጸ
ኤ.ኤች.ኤፍ ኢትዮጵያ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እየሰራ እንዳለ ገልጻል፡፡ ተቋሙ በየትምህርት ቤቶች እና ከትምህርት ቤት... read more
ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶችን ወደ ቻይና መላክ ልትጀምር መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያ የተቀቀሉ የሥጋ ምርቶች እና ተረፈ ምርቶችን ለቻይና ገበያ ልታቀርብ መሆኑን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡
የእንስሳት... read more
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሩሲያ የዩክሬን የእርቅ ስምምነት እንድትፈጽም የተሻሻለ የአጭር ጊዜ ገደብ ሰጡ
ሐምሌ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ላይ የእርቅ ስምምነት እንድትፈጽም የቀድሞውን የጊዜ ገደብ በማሳጠር፣ ከ10... read more
ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለትግራይ ልማት ማህበር የተሰጠ ማሳሰቢያ
ሙሉ መግለጫው ከታች ተያይዟል
ጉዳዩ፡ ማህበሩ በቅርቡ ያካሄደው ጉባኤን ይመለከታል
የትግራይ ልማት ማህበር (ትልማ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ... read more
ኢትዮጵያና አርጀንቲና ሪፐብሊክ የአየር አገልግሎት ስምምነት ተፈራረሙ
ጥር 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮጵያና አርጀንቲና በአየር አገልግሎት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ... read more
ከአድዋ ድል ባሻገር….
https://youtu.be/gJFVVdYp7R4
read more
የብራዚሏ ላም በአንድ ቀን 123 ሊትር ወተት በማምረት ታሪክ ሰራች
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በብራዚል የምትገኝ አንዲት ላም በአንድ ቀን ውስጥ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የወተት መጠን በማምረት የዓለም ክብረወሰን... read more
ምላሽ ይስጡ