መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ 5 ነባር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ቋንቋ የመጥፋት አደጋ ላይ በመሆኑ የመንግሥትን ትኩረት እንደሚሻ የአካባቢው ተወላጅና ፖለቲከኛው ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። እያንዳንዱ አርሶ አደር ቢያንስ አንድ ዲግሪ ያለው ልጅ ያለው መሆኑ የቦሮ ሺናሻን ማኅበረሰብ ልዩ ያደርገዋል የሚሉት ዶክተር መብራቱ፣ የብሔረሰቡ ምሁራን ቋንቋውን ለማስቀጠል የማስተዋወቅና የምርምር ሥራ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። መንግሥት ለብሔር ብሔረሰቦች መብት፣ እኩልነትና ባህላቸውን ለማስተዋወቅ የሚያደርገው ድጋፍ አበረታች ቢሆንም፣ ባህል፣ ወግና ቋንቋቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው ብሔረሰቦች ልዩ ትኩረት በመስጠት ጥናት ማድረግ እንደሚገባው ፖለቲከኛው ገልጸዋል። በተለይ ከብሔረሰቡና ከክልሉ ውጪ ለሚኖሩ የብሔረሰቡ ተወላጆች ቋንቋውን በማስተላለፍና በማስቀጠል ረገድ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ትኩረት እንደሚሻ ዶክተር መብራቱ ተናግረዋል። እንደ ማኅበረሰብ አናሳ ከሚባሉት መካከል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ተጠቃሽ ቢሆንም አናሳነቱ በቁጥር እንጂ በባህል ሀብት አይደለም የሚሉት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የባህልና ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ኃላፊ አቶ በላይ አፋ ናቸው። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አሁን ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የብሔረሰቡን ቋንቋ የመጠበቅና የማስተዋወቅ ሥራ ሊሠራ እንደሚገባው ገልጸዋል። ብሔር ብሔረሰቦች በመዲናዋ ባህላቸውንና የዘመን መለወጫ ሥርዓታቸውን እንዲያከብሩ ከመፍቀድና ከማገዝ በተጨማሪ ቋንቋና ባህላቸው የመጥፋት አደጋ ለተጋረጠባቸው በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ በመሥራት መጠበቅ እንደሚገባም ተመልክቷል። የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ከመስከረም 11 እስከ መስከረም 18 ባሉት ቀናት እየተከበረ ይውላል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በዛሬው ዕለት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት እገዛ የሚያደርጉ የክልል፣ የከተማ መስተዳድር እና የፌዴራል ተወካዮች ምርጫ እንደሚከናወን ኮሚሽኑ ገለጸ
ሐምሌ 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስልታዊ ቡድን ምክክር እስከ ትላንት ቀጥሎ እንደዋለም የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው 250... read more
ከአንጋፋዋ የኪነጥበብ ሰው #አለምጽሃይ ወዳጆ ጋር የተደረገ ቆይታ
https://youtu.be/NybH5JhdaNs
read more
ድሮኖቹ ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ #እርምጃም መውሰድ ይችላሉ ተባለ
👉የከተማዋን የፀጥታ ሁኔታና የትራፊክ ፍሰት ለመቆጣጠር ይሰማራሉ የተባሉ ድሮኖች ቁጥጥር ብቻ ሳይሆን እርምጃም እንደሚወስዱ ተገለጸ
ጥር 05 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የትራፊክ ፍሰት... read more
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር በአዲስ የተካተቱ የመንግስት ድርጅቶች ያለባቸዉን የፋይናንስ ችግሮች መለየት የሚያስችል ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ተጨማሪ የመንግስት ድርጅቶችን በስሩ እንዳከተተ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በተሰጠው... read more
ስልኩ አልተሰበረም! ከ16,000 ጫማ ከፍታ የወደቀው አይፎን! ✈️
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አስደናቂው የአላስካ ኤርላይንስ በረራ 1282 ክስተት! ከአደጋው በኋላ መርማሪዎችን ያስገረመ ክስተት ተመዝግቧል።
አውሮፕላኑ ወደ 16,000 ጫማ (5... read more
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7ኛ ዙር የክረምት ወራትም በመከናወን... read more
የፕሪቶሪያው የሠላም ስምምነት በአህጉሪቱ ያሉትን የጸጥታ ችግሮች ለመፍታት ተሞክሮ ሊወሰድበት ይገባል ተባለ
በ38ተኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጥቅምት 23/2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተከናወነው የሰላም ስምምነት ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትኤ የሚለው እሳቤ... read more
በሆቴልና መሰል ተቋማት የባለሙያዎችን አለባበስ በተመለከተ ከ50 ሺህ እስከ 1 ሺህ ብር የሚያስቀጣ ደንብ ጸደቀ
ኅዳር 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በሆቴልና መሰል ተቋማት የባለሙያዎችን አለባበስ በተመለከተ ከ50 ሺሕ እስከ... read more
ለመንግስት ሰራተኞች ይጀመራል የተባለው የጤና መድህን አገልግሎት መዘግየት የፈጠረው ቅሬታ
https://youtu.be/OZqt6p_mlJA
መንግስት የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ስራ ሲሰራ ይስተዋላል። እነዚህ ተቋማት ጥራት ላይ እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በርካታ ቅሬታዎች... read more
ሰበር ዜና፦ ኢራን በባህሬን፣ ኩዌት እና ኳታር በሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ መጠነ-ሰፊ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃት ሰነዘረች
ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፉት ሶስት ሳምንታት ሰፍኖ የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ፣ አሜሪካ በኢራን ደቡባዊ እና ምስራቃዊ ግዛቶች... read more
ምላሽ ይስጡ