መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ክልል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አራቱ የብሔረሰቡ ዞኖችና ወረዳዎች ለ15ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ ለአራተኛ ጊዜ መከበሩን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልጎሪ ተናግረዋል። የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ እንደ ሀገር እንዳለው አቆጣጠር ሁሉ 13ቱን ወራቶች መሰረት ያደረገ እንደሆነና በመስከረም ዘመንና ወቅት ተፈጥሮን ተከትሎ እንደሚከበር ተገልጿል። የጋሮ በዓል ያለ ጾታ ፣ እድሜ፣ ሃይማኖትና ብሔር ልዩነት የሚከበር መሆኑ ከሌሎች በዓላት ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል። በዓሉ በአባቶች ተመርቆ በተመረጠው ጋሪ ጀባ ወይም የጋሮ አደባባይ ላይ እንደሚከበርም አባቶች ገልጸዋል። ጋሮ ዎሮ የአዲስ ዓመት መቀበያ ብቻ ሳይሆን የይቅርታ እና የሰላም እንዲሁም የአንድነት በዓል መሆኑን ዋና አፈ ጉባኤዋ ወ/ሮ አስካለች አልጎሪ ተናግረዋል። እንደ ሀገር ሕብረብሔራዊነትን በአንድነትና በከፍታ እንዲሁም በጋራ ለማስቀጠል መሰል በዓላትን በሀገሪቱ መዲና ጭምር በድምቀት ማክበር ጠቃሚ መሆኑን በክብረ በዓሉ መድረክ ላይ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴርን ወክለው የተገኙት ከፍያለሁ አብዲሳ ተናግረዋል። በዓሉ እስከ መስከረም 18 ቀን መከበሩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
102 ዓመቱ ጃፓናዊ አዛውንት የፉጂ ተራራን በመውጣት የዓለም ክብረ ወሰን አስመዘገቡ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጃፓን የ102 ዓመቱ አዛውንት ኮኪቺ አኩዛዋ የፉጂ ተራራን በመውጣት የአለማችን ትልቁ የዕድሜ ባለፀጋ ተራራ ወጪ በመሆን... read more
ኢራን ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን አረጋገጠች
ሰኔ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢራን የፀጥታ ምክር ቤት ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱን ማረጋገጡን የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።... read more
በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ የማይሳተፉ ሃገራትን በተመለከተ ህብረቱ ሃላፊነት ወስዶ ሊሰራበት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በየአመቱ የህብረቱ መቀጫ በሆነችው አዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡
በዚህም 55 አባል ሃገራት ያሉት ህብረቱ በየአመቱ በመገናኘት የተለያዩ አህጉሩን... read more
ያላገቡ ሰራተኞች እንዲያጋቡ ቀነ-ገደብ ያስቀመጠው የቻይና ኩባንያ ለቀረበበት ትችት ምላሽ ሰጠ
እስከ መስከረም መገባደጃ ያላገቡ ሰራተኞችን ጋብቻ ካልፈጸሙ የስራ ዉል እንደሚያቋርጡ የሚያስፈራራ ፖሊሲ ያስተዋወቀው በቻይና የሚገኝ አንድ ኩባንያ ማሳሰቢያውን አንስቻለሁ ብሏል።
በምስራቅ... read more
የተፋሰሱ ሃገራት ኮሚሽን ሊቋቋም ባለበት ወቅት ግብጽ ወደ ናይል ትብብር መመለሷን ኢትዮጵያ በአጽዕኖት መከታተል አለባት ተባለ
የአባይ ውሃን በፍትሀዊነት እና በምክንያታዊነት ለመጠቀም ከ15 ዓመት በፊት የተቋቋመ የናይል ቤዚ ኢንሼቲቭ ህጋዊ ቢሆንም ግብፅ ውድቅ ማድረጓዋ እና የናይል... read more
ዛፎች እርስ በእርስ እንዳይነካኩ ራሳቸውን ይጠብቃሉ ተባለ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በተፈጥሮ ውስጥ ከሚስተዋሉ ብርቅዬና አስደናቂ ክስተቶች አንዱ የሆነው 'አክሊል መሸማቀቅ' (Crown Shyness) የተባለው ክስተት... read more
አርሰናል የሀቨርትዝን ጉዳት ተከትሎ የቶተንሀምን ዝውውር በመጥለፍ ኤብሬቺ ኤዜን ማስፈረማቸው ተረጋገጠ
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዋናነት የተውትን ዝውውር ነው በድጋሜ እየተመለሱበት የሚገኘው ተብሏል።
እንደሚታወቀው አርሰናል ባለፈው ሀምሌ ወር ከተጫዋቹ ጋር በግል... read more
የ2025 አፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ከጂቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት የማስገባት ስራ መቀጠሉ ተገለጸ
በ2025 በጀት ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ስራ እስካሁን 6 የዩሪያ እና የዳፕ ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጂቡቲ ደርሰው ጭነታቸውን በማራገፍ የአፈር... read more
ሩሲያ በኪየቭ ላይ በሰነዘረችው ጥቃት የ14 ሰዎች ሕይወት አለፈ
👉40 የሚሆኑ ሰዎች ቆስለዋል ነው የተባለው
ሰኔ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሩሲያ ፌዴሬሽን በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ ሰኞ ምሽት በሰነዘረው የአየር... read more
በአጀንዳ ልየታ ወቅት በተሳታፊዎች የተነገሩ መረጃዎችን እንደ አጀንዳ ማራገብ አግባብነት የለውም ተባለ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገራዊ ምክክሩ የአጀንዳ ልየታ ወቅት በተሳታፊዎች የሚነገሩ ጉዳዮችን እንደ አጀንዳ በመውሰድ ማሰራጨት እንደማይገባ የገለጸው የኢትዮጵያ... read more
ምላሽ ይስጡ