ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ክልሉን ወክለው ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም፣ እስካሁን የሚፈለገው ውጤት እንዳልመጣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በክልሉ አስተማማኝ እና የተረጋጋ ሰላም ባለመኖሩ ምክንያት፣ እስካሁን በቦታው በአካል ተገኝቶ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወን እንዳልተቻለ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከሕወሃት አመራር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበራት፣ ከጋዜጠኞች እና ይመለከታቸዋል ከተባሉ ሌሎች ተቋማት ጋር ከ22 ጊዜ በላይ ተደጋጋሚ ውይይቶችን ቢያደርግም፤ እስካሁን ድረስ ወደ ተግባር መግባት የሚያስችል ውጤት አልተገኘም ብለዋል።
በዚህም ምክንያት ኮሚሽኑ የመጨረሻ አማራጭን በመጠቀም፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከትግራይ ተወላጆች ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወኑን ፕሮፌሰሩ አስታውሰዋል።
በውይይቱ ላይም በቀጥታ ከትግራይ ክልል የመጡ 300 ተሳታፊዎች እና በአዲስ አበባ የሚኖሩ 400 የክልሉ ተወላጆች በጥቅሉ 700 ሰዎች መሳተፋቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ ሁሉንም አካላት ያካተተ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ በትግራይ ክልል ያለውን ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
sport
ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ መርሀ-ግብራቸው እንዲሸጋሸግ ለፕሪሚየር ሊጉ ያስገቡት ደብዳቤ ውድቅ ተደረገ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ... read more
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አዲስ አበባ ገቡ
የካቲት 07 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ... read more
የአሜሪካ የኑክሌር ሚስጥር በዲጂታል ካርዶች አማካኝነት ለዓለም ተጋለጠ!
ሚያዚያ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ባለፈው የፈረንጆች አመት ቤሊንግካት (Bellingcat) የተባለው የምርመራ ተቋም ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የአሜሪካ አየር ሃይል አባላት... read more
በኦፔክ ላይ የተጣለዉ የአሜሪካ ቀረጥ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሃገራት የነዳጅ ምርት ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ ነዉ ተባለ
የአሜሪካ ቀረጥ በተለይም ዶናልድ ትራምፕ ከተመረጡ በኋላ ያሉት ዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነቶች እንዲሁም ዓለም አቀፋዊው የንግድ ጦርነት ለተለያዩ ሃገራት ስጋት... read more
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል ያረፈበት የ24 ካራት ወርቅ ሳንቲም ሊታተም ነው
መጋቢት 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአሜሪካ የነፃነት 250ኛ ዓመት መታሰቢያን አስመልክቶ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል ያለበት ባለ 24 ካራት የወርቅ ሳንቲም... read more
በኮንትሮባንድ እና በህግ ሽፋን አማካኝነት ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ የብረታ ብረት ምርቶችን ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባሳለፍነው አመት በሃገራችን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪዎች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል መባሉን ተከትሎ በኮንትሮባንድ እና በህግ ሽፋን... read more
በኢትዮጵያ ማንነታቸው ከማይታወቁ ተቋማት ሽልማት የሚወስዱ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች እየተበራከቱ ነው ተባለ
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጥቂት የማይባሉ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪ እና አምራች ድርጅቶች ለተቋማቸው መልካም ገጽታ ግንባታ በሚል... read more
ኢትዮጵያ የወሰደችው ከናይጄሪያ ነዳጅ የማስመጣት አማራጭ ረጅም ርቀትና ከፍተኛ ወጪ የምታወጣበት ቢሆንም፣ ዓለም አቀፉን ጫና ለመቋቋም ይረዳል ተባለ
ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን የነዳጅ ምርት የማጓጓዝ ሥራ ከ40 ዓመታት በኋላ... read more
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና መሰጠት ጀመረ
በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ... read more
የአጋዥ ቴክኖሎጂ አቅርቦት ፈጣን ትኩረትን እንደሚሻ ተገለፀ
በኢትዮጵያ በአሁ ወቅት አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ የተሃድሶ ማዕከላት ቢኖሩም በቂ አለመሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቋል።
በአሁኑ ወቅት ከ22 በላይ የተሃድሶ ማዕከላት ቢሮም... read more
ምላሽ ይስጡ