ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7ኛ ዙር የክረምት ወራትም በመከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የሚተከሉት ችግኞች የደን ሽፋንን ከማሰደግ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች እንዲኖራቸው ታስቦ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ከበደ ላቀው ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡
እስካሁን እየተደረገ ባለው የችግኝ መርሃ ግብር በእቅድ ከተያዘው 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን በመጥቀስ አሁንም በመላው ሀገሪቱ መርሃ ግብሩ እንደቀጠለ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
የችግኝ መርሃ ግበሩ ሲከናወን ቦታዎቹ ላይ በባለሙያ ጥናት ተደርጎ መሆኑን እና ዘላቂነት እንዲኖራቸው እንዲሁም ቦታው ተስማሚነቱ ታሳቢ ተደርጎ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ሃምሌ እና ነሃሴ ላይ ከሚኖሩት መርሃ ግብሮች ባለፈ በአንድ ጀንበር በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በርካታ ቁጥር ያላቸው ችግኞችን የመትከል ዕቅድ መኖሩን አቶ ከበደ ገልፀዋል፡፡
መርሃ ግብሩ ከጀመረ ጀምሮ እስከ ተከላው እንዲሁም ጠቀሜታው በከተማ ብቻ ሳይሆን በክልሎችም ከፍተኛ የግንዛቤ ስራ መሰራቱን በመጥቀስ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ