ከአህጉሪቱ ወሳኝ የ2063 አጀንዳዎች ሁሉ ሰላምና ጸጥታ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ሲሉ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲሱ የህብረቱ ሊቀመንበር ጃኦ ማኑኤል ግንሳልቬስ ሎረንስ ተናገሩ።
በ2030 ከሁሉ አስቀድሞ ጥይት የማይሰማባት አፍሪካን እውን ለማድረግ ይሰራል ሲሉ አዲሱ የህብረቱ ሊቀመንበርና የአንጎላ ፕሬዝዳንት ጃኦ ማኑኤል ግንሳልቬስ ሎሬንስ ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰአት በሱዳን፣ በኮንጎና በሌሎችም የአህጉሪቱ ስፍራዎች የተንሰራፋው ነውጥ ሚሊዮኖችን ተፈናቃይ አድርጓል በማለት ጉዳዩ ትኩረት ይሻል ሲሉ ሎረንሶ አሳስበዋል።
ምላሽ ይስጡ