ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ይቆማል የሚል ግምት እንደሌለ የገለጹት የዘርፉ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
መንቀጥቀጡ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ደግሞ በመንግስትና በሚመለከታቸው አካላት በቂ ቅደመ ዝግጅት ማድረግ እንዲሁም የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችንም ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል፡፡
የስጋት ቀጠናዎችን በመለየት የቅድመ መከላከል ስራ ሊሰራ እንደሚገባ የገለጹት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ ህዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም፤ የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ናቸው፡፡
የቅድመ መከላከሉ ስራ ዜጎችን ለስጋትና መሸበር በሚዳርግ መልኩ ሳይሆን በጥናት በመመርኮዝ መሰራት እንዳለበት ነው ለጣቢያችን የተናገሩት፡፡
አሁን ላይ እየተስተዋለ ያለው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ እስከምን ድረስ ይቀጥላል፤ ምን ያህል ጉዳትስ ያስከትላል የሚለውን ለመመለስ መረጃዎችን ማጥራት ያስፈልጋል ያሉት ፕሮፌሰር አታላይ መንግስት በቂ ምላሽ መስጠት የሚያስችል ቅደመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር ዳዊት አስማረ አሁን ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው የርዕደ መሬት መጠን 10 እንደሆነ እና ይህ መጠንም አስከፊ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ንዝረቱን በቅርበት እየተከታተሉ የጉዳት መጠኑን መለየት እንደሚገባ የተናገሩት መምህሩ አሁን ላይ መንቀጥቀጡ እየተከሰተ ባለበት ፈንታሌ አከባቢ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ በዚህ ከቀጠለ መጠኑ ሊጨምር እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ በመንግስት በኩል ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች በመለየት ዜጎች ከቦታው እንዲርቁ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል፡፡
ከሰሞኑን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አዲስ አበባን ጨምሮ በአፋር እና ኦሮሚያ ክልል የተስተዋለ ሲሆን በዚህም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ