ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የውጭ ባንኮች ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅድ የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ማጽደቁ ይታወቃል፡፡
የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ደረጄ ፍቃዱ አገልግሎት ለመስጠት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ባንኮች በተቻለው መጠን ከሀገር በቀሉ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በጥምረት ወይም በአጋርነት መስራት የሚችሉበት አማራጭ ሊዘረጋ ይገባል ብለዋል፡፡
የውጭ ባንኮች ይዘውት የሚያመጡት አቅም እና ቴክኖሎጂ አሰራሩን የሚያዘምን በመሆኑ በሀገር ውስጥ ያሉ ባንኮች አሰራራቸውን በማጤን ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ መሆን የሚችሉበትን ስልት እንዲፈጥሩ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡
ነገር ግን ከውጭ የሚገቡት እና ሀገር በቀሎቹ በአጋርነት የማይሰሩ ከሆነ ዘርፉ ፈተና ላይ የሚወድቅበት አጋጣሚ እንደሚኖር ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው ለባንኩ ብሎም ለጠቅላላው የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ አብዮት የሚፈጥር እንደሆነ የሚያስረዱት ደግሞ ሌላኛው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ እዮብ አዳሙ ናቸው፡፡
ነገር ግን ባንኮቹ ሀገር ውስጥ መግባታቸው አሉታዊም አዎንታዊም ጎኖች እንዳሏቸው ነው ጨምረው የገለጹት፡፡
የውጭ ባንኮች ይዘውት የሚመጡት ሀብት ከሀገር በቀል ባንኮች ጋር የተመጣጠነ ወይም ሚዛናዊ ባለመሆኑ ውድድር ውስጥ ይከታቸዋል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል እንደ ሀገር ያለው የባንክ ኢንደስትሪ ብሎም አሰራሮች እንዲዘምኑ ሊያደርግ ይችላልም ብለዋል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበርን የጠየቀ ሲሆን ማህበሩ በቀጣይ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በማጤን ሀሳቡን እንደሚያጋራን አስታውቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ