ይህ ትዕይንት በፊልሞች እና በእሽቅድምድም ውድድሮች የተለመደ ቢሆንም፣ ጀርባው ግን የሞተር ቴክኖሎጂ እና አንዳንድ ጊዜ የአሰራር ጉድለት ውጤት ነው።
ባለሙያዎች እንደሚገልጹት መኪናዎች እሳት የሚተፉት ያልተቃጠለ ነዳጅ ወደ ጭስ ማውጫ ስርዓት አልፎ እዚያ ካለ ከፍተኛ ሙቀት ወይም ፍንጣሪ ጋር ሲገናኝ ነው።
መኪና በከፍተኛ ፍጥነት እየሄደ በድንገት ነዳጅ መስጫ ሲለቀቅ፣ ሙሉ በሙሉ ያልተቃጠለ ነዳጅ ወደ ጭስ ማውጫ ይወጣል። በጣም የሞቀው ቧንቧ ይህን ነዳጅ ወዲያውኑ ያቀጣጥለዋል።
በተርቦ መኪናዎች ላይ ደግሞ የተርቦ ፍጥነት እንዳይቀንስ ነዳጅ እና አየር ጭስ ማውጫ ውስጥ እንዲቃጠሉ ይደረጋል። ይህ የእሽቅድምድም ቴክኖሎጂ ቀጣይነት ያለው ፍንዳታ እና የእሳት ብልጭታ ይፈጥራል።
በተጨማሪም ድምጽ እና እይታ ለመጨመር የሞተር ኮምፒውተር የሚስተካከልባቸው አጋጣሚዎች አሉ። ጭስ ማጣሪያ ሲነሳም እሳቱ በግልጽ ውጭ ይታያል።
በተራ መኪናዎች ላይ የሚታይ እሳት ወይም ፍንዳታ የነዳጅ መርጫ፣ የእሳት ሻማ ወይም የቫልቭ ችግር ምልክት ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ይሻል። ከዚህም በላይ፣ ከመጠን በላይ እሳት መትፋት የጭስ ማውጫ ክፍሎችን፣ በአቅራቢያ ያሉ ፕላስቲኮችን እና ጎማዎችን ሊያቀልጥ እንዲሁም የነዳጅ ብክነትን ሊያስከትል ይችላል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ