ሕዳር 14 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) አዛሄል ሪል እስቴት በመገናኛ አካባቢ ያስገነባውን ባለ16 ወለል ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት ፕሮጀክት በስኬት አጠናቆ ለደንበኞቹ በይፋ ማስረከቡን አስታወቀ።
ድርጅቱ በሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ያስረከበው ይህ ሕንፃ፣ በእያንዳንዱ ወለል ላይ አራት አፓርትመንቶችን የያዘ ሲሆን በአጠቃላይ 64 መኖሪያ ቤቶችን አካቷል።

የመጀመሪያውን ፕሮጀክት በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ተከትሎም፣ በቦሌ ፒኮክ አካባቢ አዲስ ባለ23 ወለል ዘመናዊ አፓርትመንት ግንባታ በይፋ መጀመሩን ድርጅቱ ገልጿል። አዲሱ ፕሮጀክት የተሻለ የዲዛይን ጥራት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ምቹ የመኖሪያ አማራጮችን ይዞ እንደሚቀርብ ተመላክቷል።
በተጨማሪም አዛሄል ሪል እስቴት ጋዜጠኛ ጥበብ ሰለሞንን የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙንና የትብብር ስምምነት መፈራረሙን ይፋ አድርጓል።

የፕሮጀክቱ ርክክብ፣ የአዲሱ ሕንፃ ግንባታ መጀመር እና የብራንድ አምባሳደር ሹመቱ የድርጅቱን የእድገት ጉዞ የሚያመለክቱ ታላላቅ ምዕራፎች መሆናቸውን ሪል እስቴቱ ጠቅሶ፤ በጉዞው ውስጥ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ደንበኞቹ፣ ሠራተኞቹ፣ መሐንዲሶቹና ባለድርሻ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።

__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ