ጥቅምት 30 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና ዩናን ግዛት የሚኖረው የ24 ዓመቱ ሹ ቸንግሆንግ (Xu Chenghong) ህፃንነቱን ያሳለፈው ያለ ቤተሰብ ድጋፍ በመሆኑ፣ በሰርጉ ዕለት ጥቂት ጠረጴዛዎች እንኳን ይሞላሉ ወይ በሚል በትልቅ ስጋትና ጭንቀት ውስጥ ነበር። ተስፋ ባለመቁረጥም ምናልባት ጥቂት ደግ ሰዎች በሰርጉ ላይ ይገኙ ይሆናል በሚል እምነት በማህበራዊ ሚዲያ ጥሪ አስተላለፈ።
ሆኖም በዕለቱ የተከሰተው ነገር የሁሉንም ሰው ቀልብ የሳበ እና እጅግ አስደናቂ ነበር! የጥሪው መልእክት በኢንተርኔት ላይ በስፋት በመሰራጨቱ፣ ጥሪውን የተቀበሉ በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶች ከምግብ፣ ከቤት መገልገያ እቃዎች እና ከተለያዩ ውድ ስጦታዎች ጋር ወደ ሰርጉ ቦታ ፈሰሱ።
የመጡትን በርካታ እንግዶች አስተናግዶ ለማብላት ከ100 በላይ ሰዎች የተካተቱበት የበጎ ፈቃደኞች ምግብ አዘጋጅ ቡድን በፍጥነት የተዋቀረ ሲሆን፣ የታደመው ህዝብ ቁጥር ከአቅም በላይ በመሆኑም የሰርጉ ስነ-ስርዓት ወደ ትልቅ የአካባቢው ህዝብ አደባባይ እንዲዛወር ተደርጓል።
ይህ አጋጣሚ በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የሰው ልጅ ደግነትና መረዳዳት የጎላበት፣ እንዲሁም የብዙዎችን አንጀት የባረከ አነጋጋሪ ክስተት ሆኖ አልፏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የሴቶች ያለዕድሜ ጋብቻ እና ግርዛት የወንጀል ህግ እንዲሻሻል ለፍትህ ሚኒስቴር የማሻሻያ ጥናት መቅረቡ ተገለጸ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ የተጣለው የወንጀል ቅጣት... read more
የካሳ ክፍያ እና የፀጥታ ችግር ሀገራዊ የመንገድ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ማድረጉ ተገለጸ
እንደ ሀገር የፀጥታ ችግርና ካሳ ክፍያ የመንገድ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ማድረጉን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ተቋሙ የተበላሹ መንገዶችና... read more
የመሬት መብቶችን ማረጋገጥ ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
ታህሳስ 16 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ላንድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ (Land for Life Ethiopia) "የመሬት አስተዳደርን ማጠናከር እና የመሬት መብቶችን... read more
ያልተነካው የአርብቶ አደሩ ሀብት፤ ከባህላዊ አያያዝ ወደ ዘመናዊ ኢንቨስትመንት እንዴት ይሸጋገራል?
ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ሀብቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከቀዳሚዎቹ 10 አገራት ተርታ የምትሰለፍ ሲሆን፣ በአፍሪካ ደግሞ ቀዳሚ መሆኗ ይገለጻል። ይሁን እንጂ... read more
አባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ
ትውልዱም የሀገርን ዳር ድንበር በውል ማወቅና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር ውግንናውን ማሳየት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
አባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር አሁንም... read more
የቱሪዝም ሚኒስቴር ለ38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ በሚደረገው ቅድመ ዝግጅት በ15 ሆቴሎች የድንገተኛ ፍተሻ ማድረጉ ተገለጸ
ጥር 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው 38ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ የቱሪዝም... read more
የአውሮፓ መሪዎች ጉባኤን ተከትሎ ዴንማርክ የሁሉም ሲቪል ድሮኖች በረራ ከለከለች
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዴንማርክ በኮፐንሃገን የሚካሄደውን የአውሮፓ ኅብረት (EU) መሪዎች ጉባኤ ምክንያት በማድረግ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሁሉም... read more
ለሙት አንሳ ገዳም የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ 30 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር፣ ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው የሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም መነኮሳትን... read more
በትግራይ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ ምክንያቶች ተገፋፍተው ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ቅስቀሳ እያደረገ መሆኑን ስምረት... read more
ምላሽ ይስጡ