ጥቅምት 30 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሞት በኋላ ባለው ሕይወት እና በዕጣ ፈንታቸው ላይ ያላቸውን አመለካከት በግልጽ አስቀመጡ።
ከታዋቂው የ«60 ደቂቃዎች» (60 Minutes) መርሃ ግብር ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ ሞት እና ስለ ገነት ሲጠየቁ ያልተጠበቀ ምላሽ ሰጥተዋል።
ትራምፕ በሰጡት ቃል፦ “እንግዲህ እኔ ሃይማኖተኛ ሰው ነኝ፤ ስለዚህ በቲዎሪ ወደ ሰማይ እሄዳለሁ ብዬ አስባለሁ። ተስፋ አደርጋለሁ! ወደ ሲኦል መሄድ አልፈልግም” ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በቃለ መጠይቁ ወቅት በገነት ለመደሰት የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸውን ይቅር ማለት ይችሉ እንደሆነ ተጠይቀው፤ አሁንም በጠላቶቻቸው ላይ ያለው ቁጣ ሙሉ በሙሉ እንዳልለቀቃቸው በመግለጽ በቀላሉ ይቅር ማለት እንደሚከብዳቸው ፍንጭ ሰጥተዋል።
ይህ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እና በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ