የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ጥምረት ከዕለት ተዕለት ባህላዊ አሰራር ወጥቶ ስፖርቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማገዝ ከፍ ያለ እርምጃ ወስዷል። በዛሬው ዕለት በአሪፍ ፔይ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ ድጋፍ እና ከዳፍቴክ ጋር በመተባበር በተደረገው ታሪካዊ የሦስትዮሽ ስምምነት፣ የሀዲያ ሆሳዕና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝድ የሆነ የአባልነት መታወቂያ ማውጫ እና የማሊያ መሸጫ ፕላትፎርም ይፋ አድርጓል። እስካሁን ድረስ በአካል እየሄዱ፣ በወረቀትና በፕሪንተር እየታተመ ሰፊ ጊዜና ጉልበት የሚወስደው የደጋፊዎች ምዝገባ ሂደት አሁን ላይ በቀላሉ ሊንክ በመላክ ብቻ የሚከናወንበት ምዕራፍ ላይ ተደርሷል።

ይህ አዲስ የተጀመረው ቴክኖሎጂ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በተለይ በደቡብ አፍሪካ፣ በአረብ ሀገራት፣ በአሜሪካ እና በአውሮፓ የሚገኙ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ባሉበት ሆኖ በዲጂታል መንገድ የአባልነት መታወቂያቸውን እንዲወስዱ እና የሚወዱትን ክለብ በዶላር ጭምር እንዲደግፉ የሚያስችል ግዙፍ አቅም የፈጠረ ነው ተብሏል።
ከዚህም በላይ ደጋፊዎች በማስተር ካርድ፣ በቪዛ ካርድ ወይም በባንክ እና በሞባይል ዋሌት ክፍያቸውን ሲፈጽሙ የራሱ የQR ኮድ ያለው ዲጂታል መታወቂያ በስልካቸው ላይ በቀጥታ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ማሊያዎችን እና የተለያዩ የክለቡ ማቴሪያዎችንም ያለ ምንም እንግልት በቀላሉ መግዛት የሚችሉበትን ዕድል ተመቻችቷል።

የጥምረቱ ሰብሳቢ አቶ ደነቀው እና የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ሉብዶኖ በየነ እንደገለጹት፣ ይህ ሲስተም ክለቦች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ይገጥሟቸው የነበሩትን የፋይናንስ ግልጽነት ማጣት፣ የደጋፊዎች ትክክለኛ ቁጥር አለመታወቅ እና ስፖንሰር የማግኘት ተግዳሮቶች በታላቅ ብቃት የሚፈታ ነው።
አሪፍ ፔይ የክላውድ ሰርቪስ ወጪውን በመሸፈን እና ሶፍትዌሩን በነፃ በማበርከት ላደረገው ትልቅ አጋርነት ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፣ ይህንን ዲጂታል መድረክ ቀደም ሲል ለሀዲያ ሆሳዕና ማህበር ባደረገው መልኩ ላልሆኑትም ቀሪ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በሂደት ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ሥራ እንደሚሠራ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስን ከዘመኑ ጋር አብሮ እንዲራመድ የሚያደርገው ይህ አዲስ ጅምር፣ ለሀገር ውስጥ እግር ኳስ ኢንዱስትሪ እድገት ትልቅ መሰረት የሚጥል አበረታች ምዕራፍ ሆኖ ተመዝግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ