መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ የተጣለው የወንጀል ቅጣት እጅግ አነስተኛ በመሆኑ እንዲሻሻል የህግ ማሻሻያ ጥናት ለፍትህ ሚኒስቴር መቅረቡ ተገልጿል። በወንጀል ህጉ የተቀመጠው የሴት ልጅ ግርዛት ቅጣት የሦስት ወራት እስራት እና የ500 ብር የገንዘብ መቀጮ ብቻ መሆኑን በመጥቀስ፣ ይህ የድርጊቱን ፈጻሚዎች የሚያስተምር እና መጣኝ ባለመሆኑ ጥናቶችን በማድረግ ህጉ እንዲሻሻል ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩን በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት ጥበቃና ምላሽ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ አለሙ ወርቁ ተናግረዋል። ጉድለት ያለባቸውን ህጎች የመለየቱ ሥራ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት የተሳተፉበት መሆኑን ጠቅሰዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህግ ማሻሻያ ባለፈ በግል በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚሰሩ የተለያዩ ማህበራት ጋር በጋራ በመስራቱ አሁን ላይ ለሚታዩ መሻሻሎች ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አብራርተዋል። ችግሩ እጅግ አሳሳቢ በመሆኑ በመንግስትም ሆነ በግል በሚንቀሳቀሱ ማህበራት በኩል የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመልከቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በኢፌዴሪ አየር ኃይል ውስጥ የተሰራችው ፀሃይ – 2 የተሰኘች አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት ማጠናቀቋ ተገለጸ
በኢፌዴሪ አየር ኃይል ውስጥ የተሰራችው ፀሃይ - 2 የስልጠና አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት ማከናወን መቻሏን አየር ኃይሉ አስታውቋል፡፡
ፀሃይ -2... read more
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ አውቶብስ የታክሲ አገልግሎት ማስጀመሩን ገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት መዲናዋ ላይ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ለመቀነስ በ10 የተመረጡ ቦታዎች ላይ የከተማ አውቶቡስ የታክሲ... read more
በሕፃፅ መጠለያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተላከው የዕርዳታ እህልና ገንዘብ የት ገባ?
ታህሳስ 14 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሕፃፅና አካባቢው በመጠለያ የሚገኙ ማህበረሰቦች በከፍተኛ የረሃብና የችግር አዙሪት ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ላለፉት አራት... read more
የኃይል ሥርቆት በፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና... read more
የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ መኖሩን የማያውቁ ተቋማት መኖር የአካል ጉዳተኞች አካታችነት ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነዉ ተባለ
በሃገራችን የአካል ጉዳተኞች የስራ ስምሪት አዋጅ ቢኖርም አሁንም የሚታየው የስራ ስምሪት የአካል ጉዳተኛ ሰራተኛውን ያማከለ አሰራር ባለመኖሩ ያለውን የግንዛቤ ክፍተት... read more
አስደናቂ የጦር ጀቶች
👉ራፋል እና ዩሮፋይተር ታይፎን በንፅፅር
ሰኔ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እነዚህ ጀቶች የዘመናዊ የአየር ላይ ውጊያ ምሳሌዎች ሲሆኑ፣ በተለያዩ አገራት አየር... read more
ኢትዮቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት 235 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስታወቀ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት አመት 162 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ማስታወቁ ይታወሳል።
በ2018 በጀት አመት በገጠርና... read more
የዩኤንኤድስ (UNAIDS) ሪፖርትና በአፍሪካ ሴቶች ላይ ያለው አደጋ
የተባበሩት መንግሥታት የኤድስ መከላከል ፕሮግራም (ዩኤንኤድስ) ዓለም አቀፍ የኤድስ ቀንን አስመልክቶ ይፋ ባደረገው የ2025 ሪፖርት፣ በኤድስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ2010... read more
በጃፓን የንቦች ቁጥር እየቀነሰ በመሆኑ የሮቦት ንቦች ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው ተባለ
ነሐሴ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም ዙሪያ የንቦች ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ ምክንያት በሰብል ምርት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመከላከል ጃፓን... read more
በሀገሪቱ ያሉትን አጠቃላይ የወተት ማቀነባበሪያዎችን የምርት ጥራት ማረጋገጥ የሚችል ቤተሙከራ ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ
ወደ 25 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ወጪ በማድረግ፣ በማቀነባበሪያው የሚያልፉ ወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች ጥራታቸው እንዲረጋገጥ እየተደረገ መሆኑን የሰበታ አግሮ... read more
ምላሽ ይስጡ