መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይ እና የስፖርት ተንታኝ ጋሪ ኔቪል በፉልሃም ጨዋታ ወቅት በማይክል ካሪክ ቡድን ላይ ከባድ ትችት የሰነዘረ ሲሆን፣ ማንቸስተር ዩናይትዶች በሜዳ ውስጥ በሚያሳዩት እጅግ ዝግ ያለ አካሄድ እና የፍላጎት ማነስ ከቀጠሉ በአሰልጣኝ ካሪክ ስር ምንም አይነት ስኬት ማሳካት እንደማይችሉና ቡድኑም የትም እንደማይደርስ አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። ኔቪል በክራቨን ኮቴጅ በነበረው ጨዋታ የዩናይትድ ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ሲራመዱ የታዩበትን የመጀመሪያዎቹን 15 ደቂቃዎች እሱ ከተመለከታቸው “እጅግ አሳዛኝ እና ከፉ 15 ደቂቃዎች” ሲል የጠራቸው ሲሆን፣ ቡድኑ ያለው የጨዋታ ተነሳሽነት ዝቅተኛ መሆን አሳሳቢ እንደሆነ አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በማጥቃት ላይ ያተኮረ እንቅስቃሴ ቢታይምና በሁለቱ ክለቦች በድምሩ 26 የግብ ሙከራዎች ቢደረጉም፣ የመጀመሪያው አጋማሽ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። በዚሁ አጋማሽ የዩናይትዱ የክንፍ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ሁለት ወሳኝ የግብ እድሎችን ሳይጠቀምባቸው የቀረ ሲሆን፣ የፉልሃሙ ግብ ጠባቂ በርንድ ሌኖ በበኩሉ ሁለት ድንቅ ኳሶችን በማዳን የዩናይትድን ሙከራዎች አክሽፏል። ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ማንቸስተር ዩናይትድ ሊጉ ከተጀመረ ባደረጋቸው 5 ጨዋታዎች 5 ነጥብ በመሰብሰብ 12ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
አሪያና ሳባሌንካ እና ያኩፕ ሜንሲክ የማዬሚ ኦፕንን አሸነፉ
ዘንድሮ ለ40ኛ ጊዜ በተከናወነው አመታዊው የማዬሚ ኦፕን ሜዳ ቴኒስ ውድድር በአሜሪካ ማዬሚ ግዛት ላይ ሲከናወን በሴቶች የአለም ቁጥር አንዷ አሪና... read more
የሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዳሰሳ
በየአመቱ ከሚከናወኑ እና የክለቦች ፉክክር ከሚደምቅበት እንዲሁም በአውሮፓ ውስጥ ሀያሉ ክለብ ለመባል የሚደረግ የክለቦች ትንቅንቅ በተለያዩ የአውሮፓ ግዙፍ ስቴዲየሞች በባውዛ... read more
ሩበን አሞሪም ለማርከስ ራሽፈርድ ንግግር ምላሽ ሰጡ
ታኅሳስ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በማንቸስተር ዩናይትድ ቤት እህል ውሀው ሊያበቃ ከጫፍ የደረሰው የ27 አመቱ እንግሊዛዊ እኔ በግሌ ክለቡን ለቅቄ አዲስ... read more
ማንቸስተር ሲቲዎች ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገለጸ
ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ሲቲዎች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የኤቨርተኑን ኢሊማን ንዲያዬን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ጋዜጠኛ ቤን... read more
የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ የቦክስ ፍልሚያ የሚደረግበት ቦታ እና ጊዜ ታወቀ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ለዓመታት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ የከባድ ሚዛን የቦክስ ውድድር... read more
ቲዮ ኸርናንዴዝ ሚላኖች እሱን ባስተናገዱበት መንገድ ደስተኛ አለመሆኑን ለወኪሉ አሳውቋል ተብሏል
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ፈረንሳዊ የቡድኑ አምበል የኮንትራት ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነ ይታወቃል። በ2026 ውሉ ይጠናቀቃል ስለዚህ ውሉን እንዲያድስ... read more
ሊቨርፑል ሚሎሽ ኬርኬዝን ሁለተኛ ፈራሚያቸው ለማድረግ ተቃርበዋል
ይሄ ሀንጋሪአዊ በ2023 ሰኔ ወር ላይ በርንማውዝን ከተቀላቀለ በኋላ በጣም አስደናቂ የግል አቅሙን እያስመለከተ ይገኛል። በዛ ላይ ገና 20 አመቱ... read more
ራፊኛ እስከ 2030 ከባርሴሎና ጋር የሚያቆየውን ውል ማደሱ ተሰምቷል
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዘንድሮ እጅግ በጣም አስደናቂ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የብሉግራናዎቹ አምበል እና የፊት መስመር ተጫዋች... read more
ካርሎስ አልካራዝ አስደናቂ ድል በማስመዝገብ የግራንድ ስለም ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ
በታሪክ ረጅም ሰአት የፈጀው የሮላንድ ጌሮስ የፈረንሳይ ሜዳ ኦፕን ቴኒስ የፍፃሜ ውድድር በስፔናዊው ተስፈኛ የሜዳ ቴኒስ ተወዳዳሪ ካርሎስ አልካራዝ አሸናፊነት... read more
ፊዮሬንቲና ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረቡ ተገለጸ
ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጣሊያኑ ክለብ ፊዮሬንቲና የ25 ዓመቱን የማንቸስተር ዩናይትድ እና የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን ለማስፈረም... read more
ምላሽ ይስጡ