መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሀገሪቱ ከሚገኙ አካል ጉዳተኞች መካከል 11.8 በመቶ ያህሉ ብቻ የትምህርት ዕድል እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ብሔራዊ ማኅበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብሬ ተሾመ ተናግረዋል። የትምህርት ዕድል ያላገኙ ሕፃናትና አካል ጉዳተኞች ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነና ሽፋኑ አሁንም ዝቅተኛ መሆኑን ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩም ገልጸዋል። ወላጆች አካል ጉዳተኛ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ ከመላክ አንጻር ክፍተት እንዳለባቸው የተናገሩት ኃላፊው፤ ወላጆች ይህንን ችግራቸውን በመቅረፍ ልጆቻቸውን የማስተማር ቀዳሚ ኃላፊነት እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም ብለዋል። የትምህርት ዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም በሚያካሂዱት የቅኝትና የቁጥጥር ሥራ ወቅት፤ በየአካባቢው ካሉ አካል ጉዳተኞች ምን ያህሉ ትምህርት ቤት እንደገቡ ሊከታተሉና አስፈላጊውን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ከአማራ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ያሳተማቸውን የብሬል መጻሕፍት ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች ተደራሽ ቢያደርግም በቂ እንዳልሆነ የሚናገሩት አቶ ገብሬ፤ የማኅበሩ ግዴታ መንግሥት ይህንን እንዲያሟላ መጠየቅ ቢሆንም፣ አንዳንድ የመንግሥት አካላት ሳይቀሩ ማኅበሩ እንዲያሟላ ሲጠይቁ ይስተዋላል ብለዋል። የትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያስፈልጉ የትምህርት ግብዓቶችን በሚፈለገው ልክ ማቅረብ እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡ የአካል ጉዳተኞችና የመምህራን ማኅበራትን ጨምሮ ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት፣ አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ዜጋ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ላሚን ያማል ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ተረጋገጠ
ሕዳር 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔን ብሔራዊ ቡድን እና የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ በላሚን ያማል ጉዳይ የገቡበት ውዝግብና አለመግባባት እንደቀጠለ... read more
የአካል ጉዳተኞችን የስራ እና የገበያ ትስስር ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ይቀርፋል የተባለ የዲጂታል ስልጠና ስርዓተ ትምህርት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሊሰጥ መሆኑ ተገለጸ
አካል ጉዳተኞች ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን በማስተዋወቅ እና ለገበያ በማቅረብ ሒደት የሚገጠሟቸውን ችግሮች መቅረፍ የሚስያችል የዲጂታል ስልጠና ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በቴክኒክና... read more
ሱዳን የዓባይ ወንዝ የውሃ መጠን እየጨመረ እንደሚሄድ እና የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥማት እንደሚችል አስታወቀች
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአባይ ወንዝ ከፍታው ሲጨምር የአገሪቱ መንግስት ለህዝቡ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላልፋል።
በመሆኑም አገሪቱ ትላንት ማክሰኞ በአባይ ወንዝ... read more
አፍሪካ ዉስጥ በጎች እና ፍየሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰውን አስከፊ ቫይረስ (ፔስቴ ዴስ ፔቲትስ ሩሚናንት)(PPR) ለመዋጋት የፓን አፍሪካን ፕሮግራም ተጀመረ
አዲስ አበባ በጥር ወር መጨረሻና በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ የአፍሪካ ህብረት ታላላቅ ግቦች እና የፓን አፍሪካ አጀንዳዎች ጋር የተጣጣሙ ወሳኝ... read more
ግማሽ ጭንቅላቷን ብታጣም ተስፋ አልቆረጠችም፦ የክሪስቲና ሳንታውስ አስገራሚ የሕይወት ታሪክ
መጋቢት 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በስምንት ዓመቷ ሕይወቷን አደጋ ላይ የሚጥልና በቀን እስከ 150 ጊዜ የሚደርስ የሚጥል በሽታ (seizure) ያጋጥማት... read more
መንግስት የኢኮኖሚ እድገቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥና የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ
ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) መንግስት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥና የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ የኢፌድሪ መንግስት... read more
ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ወሳኝ ኩነቶቻቸውን በመደበኛው የምዝገባ ስርዓት በማስመዝገብ ህጋዊ እውቅናና ጥበቃ እያገኙ ነው ተባለ
ነሐሴ 15 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ወሳኝ ኩነቶቻቸውን በመደበኛው የምዝገባ ስርዓት በማስመዝገብ... read more
በፀሐይ ኃይል የሚሰራው ግዙፉ የመኪና ማጓጓዣ መርከብ የመጀመሪያ ጉዞውን አጠናቀቀ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለማችን ትልቁ በፀሐይ ኃይል የሚሰራ የመኪና ማጓጓዣ መርከብ "ዩዋን ሃይ ኮው" (Yuan Hai Kou) የመጀመሪያ ጉዞውን... read more
ፓሪስ ሴንት ጄርሜ ሞሀመድ ሳላህን ለማስፈረም ይፋዊ ንግግር መጀመሩን የፈረንሳዩ ጋዜጣ ሌኪፕ ዘግቧል
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ32 አመቱ ግብፃዊው ኮከብ ሞሀመድ ሳላይ የፈረንሳዩን ሀያል ክለብ ለመቀላቀል ይፋዊ በሆነ መልኩ ንግግሮችን መጀመሩ... read more
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ከመስፋፋቱ አስቀድሞ፣ ቴክኖሎጂውን የሚመራውን የሰው ሃይል ዝግጁነት መጠየቅ ይገባል ተባለ
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በፋይናንስ ዘርፍ የቴክኖሎጂ ለውጥና የሰው ኃይል ዝግጁነትን በሚመለከተው FinHuman 2026 መድረክ፣ የወደፊቱን የሥራ ዓለም ለመምራት... read more
ምላሽ ይስጡ