ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታሪክ ሰነዶች ውስጥ ሰፍረው ከሚገኙ እጅግ አጃኢብ የሚያስብሉ ክስተቶች መካከል አውስትራሊያ በ1932 እ.ኤ.አ ከሰራዊቷ በተጨማሪ መግደያ መሳሪያዎችን በመታጠቅ ከግዙፎቹ የእሙ (Emu) አእዋፍ ጋር ያደረገችውና ሳይሳካላት የቀረው ወታደራዊ ዘመቻ አንዱ ነ
በወቅቱ በሺዎች የሚቆጠሩ እሙዎች በምዕራብ አውስትራሊያ የሚገኙ የእርሻ ማሳዎችን በመውረር የገበሬዎችን ሰብል ያወደሙ፣ አጥር ያፈረሱ እና ከፍተኛ ውድመት ያደረሱ በመሆናቸው መንግስት ወታደሮቹን ከባድ መካነ-መድፎችና መሣሪያዎች አስታጥቆ ዘመቻ አስጀምሮ ነበር።
ነገር ግን ወታደሮቹ አእዋፉን በቀላሉ ለማጥፋት አቅደው ቢነሱም፣ የእሙ አእዋፍ በከፍተኛ ፍጥነት የመሮጥ፣ የመበታተን እና የተኩስ አቅጣጫን የማዞር አስደናቂ ችሎታ በማሳየታቸው ዘመቻው ሳይሳካ ቀርቷል።
ብዙ በጥይት የተመቱት አእዋፍ እንኳን ሳይወድቁ ማምለጣቸውን ተከተሎ፣ በርካታ ጥይቶች በከንቱ መባከናቸውን የተረዱት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ዘመቻውን በአጭሩ ለማቆም እና ወታደሮቻቸውን ለማስወጣት ተገደዋል።
ይህ ታሪካዊ ክስተት ዛሬ ላይ “የእሙ ጦርነት” (Emu War) በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ባደረገው ፍልሚያ ያልተጠበቀ ሽንፈት አስተናግዶ የተመለሰበት አስቂኝ እና ድንቅ የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ይወሳል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ዩቲዩብን ከለከለች
ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአውስትራሊያ መንግስት ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ዩቲዩብ አካውንት እንዳይኖራቸው የሚያግድ አዲስ ህግ ይፋ አድርጓል። ይህ... read more
ከአናናስ ቅጠል የሚዘጋጅ ቆዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት አገኘ
መስከረም 07 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአካባቢ ላይ በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት፣ ከአናናስ ቅጠሎች የሚሰራ አዲስና ፈጠራ የተሞላበት ቁሳቁስ በአለም አቀፍ... read more
የመምህራን የገቢ ምንጭና አቅም አነስተኛ መሆኑ ቢታወቅም መርህን ለመከተል ያህል ሃብት ማስመዝገቡ ተገቢ መሆኑ ተገለጸ
የመምህራን የገቢ ምንጭና አቅም አነስተኛ መሆኑ ቢታወቅም መርህን ለመከተል ያህል ሃብት ማስመዝገቡ ተገቢ መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስታውቋል።
መምህራን ከእለት ገቢ... read more
“የእሳት ጭልፊት” ተብለው የተሰየሙት አእዋፍ
🔰የእሳት አደጋ መንስኤ ወይስ ብልህ አዳኞች?
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)"የእሳት ጭልፊት" ተብለው በሚጠሩ አዳኝ አእዋፍ ዙሪያ አስደናቂ እና አሳሳቢ ክስተት... read more
ከማሰልጠኛ የትምህርት ተቋማት የሚወጡ መምህራኖች ቢኖሩም በእንግሊዘኛ የትምህርት ዘርፍ ላይ ለመሰማራት ፍቃደኝነታቸውን እያሳዩ አይደለም ተባለ
መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከቀናት በፊት የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለመገናኛ ብዙሃኑ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ካነሷቸው... read more
የመስቀል እና ኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ ሆቴሎች ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም ወር ላይ የሚከበሩትን የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን ለመታደም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቱሪስቶች... read more
የፈረንጆች አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ
ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017... read more
በክልሉ በምሽትና በርቀት ተምረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 23 ሺህ 281 ተማሪዎች ውስጥ አንድም ተማሪ የማለፊያ ውጤት አለማምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በምሽትና በርቀት በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ተከታትለው... read more
የመኪናዎ ጎማ ላይ ያሉትን ምስጢራዊ ቁጥሮች እና ፊደላት ያውቋቸዋል?
ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የመኪና ባለቤቶች እና አሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው ጎማ ሲገዙ ወይም ሲቀይሩ በጎማው ጎን (Sidewall) ላይ የተጻፉትን ቁጥሮች... read more
ለ57ሺህ ታዳጊ ወጣቶች የክረምት የስፖርት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ለ57ሺህ ታዳጊ ወጣቶች የክረምት የስፖርት ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
ምላሽ ይስጡ