ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የመኪና ባለቤቶች እና አሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው የሞተር ዘይት ሲገዙ ወይም ሲቀይሩ በዘይቱ መያዣ ላይ የተጻፉትን ቁጥሮች እና ፊደላት ትርጉም ማወቅ የሞተሩን እድሜ ለማራዘም ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ። እነዚህ ምልክቶች የዘይቱን ውፍረትና ቅጥነት (Viscosity)፣ የአየር ንብረት ተስማሚነት እና የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የሚገልጹ መረጃዎች ናቸው።
ለአብነት ያህል SAE 5W-30 API SP የሚለውን የሞተር ዘይት ላይ ያለ ምልክት ብንመለከት ትርጉሙ እንደሚከተለው ይብራራል፦
የውፍረትና ቅጥነት መጠን (Viscosity Grade – SAE)
የመጀመሪያው 5W የሚያመለክተው ዘይቱ በብርድ ወይም በቅዝቃዜ ወቅት ያለውን የቅጥነት ደረጃ ነው። W የሚለው ፊደል Winter (ክረምት/ቅዝቃዜ) የሚለውን የሚያስረዳ ሲሆን ከ W በፊት ያለው ቁጥር አነስተኛ በሆነ መጠን ዘይቱ በቅዝቃዜ ወቅት በፍጥነት በመፍሰስ ሞተሩ ሲነሳ ወዲያውኑ የመጠበቅ አቅሙ ከፍተኛ ይሆናል።
ከዳሽ ( – ) በኋላ ያለው 30 ቁጥር ደግሞ ሞተሩ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ በሚሰራበት ወቅት የሚኖረውን የዘይት ውፍረት ያሳያል። ይህ ቁጥር ከፍ ባለ ቁጥር ዘይቱ በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ውፍረቱን ሳይለቅ የመጠበቅ አቅሙ የጎላ ይሆናል።
በመቀጠል የሚገኘው API SP የሚለው ምልክት የሰሜን አሜሪካው የፔትሮሊየም ኢንስቲትዩት የጥራት ማረጋገጫ ነው። API ከሚለው ጽሁፍ ቀጥሎ የሚመጣው የመጀመሪያው ፊደል S ከሆነ ዘይቱ ለቤንዚን (Petrol) ሞተር የተሰራ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን C ከሆነ ደግሞ ለዲዘል (Diesel) ሞተር የሚያገለግል ነው።
ከ S ወይም C ቀጥሎ የሚመጣው ሁለተኛው ፊደል (ለምሳሌ SP) የቴክኖሎጂውን አዲስነትና የጥራት ደረጃ ያመለክታል። በፊደላት ቅደም ተከተል መሰረት ሁለተኛው ፊደል ወደ Z በጠጋ ቁጥር ዘይቱ ዘመናዊና ከፍተኛ የሞተር መከላከል አቅም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።
በተጨማሪም በዘይቱ መያዣ ላይ Full Synthetic የሚል ጽሁፍ ካለ ዘይቱ በላቦራቶሪ የተሰራና ረጅም ርቀት የሚያስኬድ ሲሆን፤ Semi-Synthetic ከሆነ ደግሞ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ዘይት ቅልቅል ነው። Mineral Oil የሚለው ደግሞ ከተፈጥሮ ድፍድፍ ነዳጅ የተጣራና በየአጭር ርቀቱ መለወጥ የሚኖርበት መሆኑን ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ለነዳጅ እጥረት እንደምክንያት እየቀረበ ያለው ጉዳይ
https://youtu.be/y9xV3WV4Koo
read more
የልጆች አስተዳደግ የነጠላ ቤተሰብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የመላው ማህበረሰብ የጋራ ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ የሚያሳስበው «ልጆቻችን አይሰሙንም፤ ያዩናል እንጂ» የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ በትናንትናው ዕለት ተመረቀ
በዶክተር መዝገብ ገደፌ የተደረሰው ይህ መጽሐፍ ይፋዊ የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱን በቤልኤር አካባቢ በሚገኘው ራስ አምባ ሆቴል አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ... read more
የሀበ-ጋር የክርክር መድረክ” በገንዘብ እጥረት ምክንያት ለጊዜው ቢቋረጥም፣ የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ ካገኘ ውይይቶቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ
በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዴሞክራሲ ባህልን ለማሳደግና በፖለቲካዊ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ፍጭት እንዲኖር ከሚሰሩ የመወያያ መድረኮች መካከል አንዱ... read more
ፕሪሚየር ሊጉ የትኛውም ቡድን የPSr ህግጋቶችን አልጣሰም በሚል የነጥብ ቅጣት እንደማያስተላልፍ አሳውቋል
ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የትርፋማነት እና ይዘት ክፍፍል በተለይ ደግሞ ወጪ እና ገቢያቸውን በማያመጣጥኑ ክለቦች ላይ ፕሪሚየር ሊጉ የነጥብ ቅጣት... read more
ሱዳን የዓባይ ወንዝ የውሃ መጠን እየጨመረ እንደሚሄድ እና የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥማት እንደሚችል አስታወቀች
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአባይ ወንዝ ከፍታው ሲጨምር የአገሪቱ መንግስት ለህዝቡ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላልፋል።
በመሆኑም አገሪቱ ትላንት ማክሰኞ በአባይ ወንዝ... read more
ሚዲያዎች በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን የመረጃ ፍሰት በሰላማዊ መንገድ በማስተዳደር ለህዝቡና ለሃገሪቱ የሚበጁ ዘገባዎችን በሃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በፖለቲካዊ ሁኔታዋ ላይ እያለፈች ባለችው ወሳኝ ጊዜ ሚዲያዎች በሃላፊነት እና በተጠያቂነት መረጃ ማቅረብ እንዳለባቸው ምሁራን ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
♻️ስርቆት የፈጸሙ ግለሰቦች ተይዘዋል
👉የቃሉ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ከኮምቦልቻ ቁጥር 2 እስከ ኮምቦልቻ ቁጥር 1 በተዘረጋ 132 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ታወር ላይ ስርቆት... read more
ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን መጠጦች በብዛት መውሰድ ለፀጉር መርገፍ ሊያጋልጥ ይችላል
👉አዲስ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ በስኳር የበለጸጉ መጠጦችን በየጊዜው መውሰድ በተለይም ለወንዶች የፀጉር መሳሳት ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል።
ሕዳር 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተመራማሪዎች... read more
በሀገር ውስጥ ታክሞ መዳን ለምን አስቸጋሪ ሆነ?
👉
https://youtu.be/67lTpwIJ3X0
read more
ህንድና ካናዳ ከ10 ወራት በኋላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለማደስ አዲስ ከፍተኛ መልዕክተኛ ሰየሙ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ህንድ እና ካናዳ ለ10 ወራት ያህል ተቋርጦ የቆየውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማደስ የሚያስችላቸውን አዲስ መልዕክተኞች... read more
ምላሽ ይስጡ