ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው የባህር ኃይል ክፍሏን በታክቲካል የኒውክሌር መሳሪዎች ለማስታጠቅ እና ይበልጥ ግዙፍ የሆኑ ዘመናዊ የጦር መርከቦችን ለመገንባት በከፍተኛ ፍጥነት እየሰራች መሆኑን በይፋ ተናገሩ። መሪው ይህንን ያሉት ሀገሪቱ ባለፈው ዓመት የገነባቻቸው እና በሬክተር ስኬል 5 ሺህ ቶን የሚመዝኑት ሁለት ግዙፍ አጥፊ የጦር መርከቦች መካከል አንደኛዋ የሆነችው “ቾይ ሂዮን” (Choe Hyon) በይፋ ስራ በምትጀምርበት የሹመት ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።
ኪም ጆንግ ኡን በናምፖ የወደብ ከተማ በተካሄደው በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ እንደገለጹት፤ የባህር ኃይሉን በኒውክሌር የመሳሪያ ስርዓቶች የማደራጀቱ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ያለምንም መስተጓጎል በተያዘለት መስመር እየተጓዘ ይገኛል። ይህ እርምጃ የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር ኃይል ለማንኛውም ዓይነት ሁለገብ እና ፈጣን ወታደራዊ እርምጃ ዝግጁ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን መሪው በኩራት ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሀገሪቱ በየዓመቱ ሁለት ግዙፍ የጦር መርከቦችን የምትገነባ ሲሆን፥ ወደፊትም እስከ 10 ሺህ ቶን የሚመዝኑ እጅግ ግዙፍ ስልታዊ የጦር መርከቦችን በቅደም ተከተል ወደ ስራ እንደምታስገባ ይፋ አድርገዋል።
ሰሜን ኮሪያ ቀደም ሲል ባወጣችው መግለጫ አዲሷ “ቾይ ሂዮን” የተባለችው የጦር መርከብ የሀገሪቱን እጅግ “ኃያላን መሳሪዎች” የታጠቀች መሆኑን ያረጋገጠች ሲሆን፥ መርከቧ የኒውክሌር ዶንጓዴዎችን እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን ጭኖ የመተኮስ ከፍተኛ አቅም እንዳላት ተገልጿል። ይህ በሰሜን ኮሪያ በኩል የታየው አዲስ የባህር ኃይል መዋቅር ሽግግር በአከባቢው በአሜሪካ እና በደቡብ ኮሪያ የሚደረጉ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የታለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ የኪም ጆንግ ኡን አዲስ ወታደራዊ አዋጅ በኮሪያ ባህረ-ሰላጤ ላይ ያለውን የደህንነት እና የፖለቲካ ውጥረት ይበልጥ ወደ ከፋ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ የተፈራ ሲሆን፥ በጉዳዩ ዙሪያ የሚወጡ አዳዲስ ዝርዝር መረጃዎችን እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በምርጫ ህጉ የሚጠበቁ ማሻሻያዎች ምንድናቸው?
👉
https://youtu.be/NgfOdRJMnM0
read more
81 በመቶ የሚሆኑ የንግድ ባንክ ደንበኞች የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለ
ታኅሳስ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ዲጂታል ፋይናንስን ለማስፋፋት ካቀደው እቅድ ቀድሞ ማሳካት መቻሉን አመላክቷል፡፡
የዲጂታል ስርዓቱ መስፋፋት በአገልግሎት አሰጣጥ ሒደት... read more
የዓለም ኃያላን በንፅፅር፡ ቻይና ወይስ ዩኤስ? (በጀት፣ አውሮፕላን እና ኑክሌር)
ሕዳር 10 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለምን ጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምህዳር የሚመሩት ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ቁልፍ ዘርፎች ያላቸው ብቃት... read more
በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀድሞው ቦታቸው የመመለስ ስራ መጀመሩ ተገለጸ
ሰኔ 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ምክንያት ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመጠለያ ጣቢያ በማስወጣት ወደ ቀድሞ ቦታቸው... read more
ለጎረቤት ሀገራት ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዎች ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ ያስፈልጋል ተባለ
በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል ያለዉን አዎንታዊ ግንኙነት በሚያሳይ መልኩ እና በኤርትራ በኩል ያለውን ነባራዊ ጠብ ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ብስለት በሚስተዋልበት ዲፕሎማሲያዊ... read more
የ12 ዓመቷ ታዳጊ የፈጠራ ስራ የዓለምን ትኩረት ሳበ፤ ለትምህርት ቤቶች የሚሆን 11.5 ሚሊዮን ዶላር በጀትም አስገኘ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በትምህርት ቤቶች ውስጥ የአየር ጥራትን ለማሻሻልና የአየር ወለድ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ የሚረዳ ዝቅተኛ ወጪ የሚጠይቅ የአየር... read more
በኢትዮጵያ በቅርቡ በተደረገ ጥናት 37 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳልሆነ ተገለጸ
ሰኔ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ በቅርቡ በተደረገ ጥናት እስካሁን ካለው የህዝብ ቁጥር የዜሮ አምፖል ተጠቃሚዎችን ጨምሮ 63 በመቶ የሚሆነው... read more
በትግራይ እንዴት ሰላም ይስፈን? 👉
https://youtu.be/C9t7w_FLFSI
read more
ከአደጋ ቁጥሮች በስተጀርባ ያሉ ህይወቶች፡ በኢትዮጵያ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ መዋቅራዊ ለውጥ ለምን ያስፈልጋል?
በየእለቱ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ዜናዎች ላይ “በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ” የሚሉ መርዶዎችን መስማት የተለመደ የዕለት ተዕለት ክስተት ሆኗል። ነገር... read more
በመዲናዋ የዳቦ መሸጫ ዋጋን የማረጋጋት እና ከግራም በታች እንዳይሸጥ የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ መሆኑን የንግድ ቢሮ አስታወቀ
ሰኔ 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የዳቦ መሸጫ ዋጋ መጨመር እና የግራም መቀነስ እንደሚስተዋል በማህበረሰቡ በኩል ቅሬታ ይቀርባል።
ይህንን... read more
ምላሽ ይስጡ