ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ክልሉን ወክለው ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም፣ እስካሁን የሚፈለገው ውጤት እንዳልመጣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በክልሉ አስተማማኝ እና የተረጋጋ ሰላም ባለመኖሩ ምክንያት፣ እስካሁን በቦታው በአካል ተገኝቶ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወን እንዳልተቻለ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከሕወሃት አመራር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበራት፣ ከጋዜጠኞች እና ይመለከታቸዋል ከተባሉ ሌሎች ተቋማት ጋር ከ22 ጊዜ በላይ ተደጋጋሚ ውይይቶችን ቢያደርግም፤ እስካሁን ድረስ ወደ ተግባር መግባት የሚያስችል ውጤት አልተገኘም ብለዋል።
በዚህም ምክንያት ኮሚሽኑ የመጨረሻ አማራጭን በመጠቀም፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከትግራይ ተወላጆች ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወኑን ፕሮፌሰሩ አስታውሰዋል።
በውይይቱ ላይም በቀጥታ ከትግራይ ክልል የመጡ 300 ተሳታፊዎች እና በአዲስ አበባ የሚኖሩ 400 የክልሉ ተወላጆች በጥቅሉ 700 ሰዎች መሳተፋቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ ሁሉንም አካላት ያካተተ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ በትግራይ ክልል ያለውን ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በ2019 በጀት ዓመት በአንድ በመቶ የተቋማት ድጋፍ ከ6 ሺህ በላይ ሕፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ተባለ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ ድጋፍ እና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገለፃል። እነዚህን ሕፃናት ለመርዳት... read more
አስትሮይድ በ2032 ጨረቃን ሊመታ ይችላል
👉የምድር ሳተላይቶችም ሊጎዱ ይችላሉ ተባለ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቀደም ሲል ምድርን ሊመታ ይችላል ተብሎ ሲሰጋ የነበረው አስትሮይድ 2024 YR4፣ አሁን... read more
የህጻናት ፍትህ የማግኘት መብት ተገቢ ትኩረት እያገኘ አለመሆኑ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ
ህጻናት ለሚገባቸው ፍትህ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ረገድ የሚመለከታቸው አካላት በቅጡ እየሰሩ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
ዛሬም... read more
በገና በዓል ከ50 በላይ አሸከርካሪዎች ጠጥተው ሲያሽከረክሩ መገኘታቸውና መቀጣታቸዉ ተገለጸ
ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በ9ኙ ክፍለከተሞች በተመረጡ ቦታዎች በተካሄደ ቁጥጥር የአልኮል ትንፋሽ ምርመራ ከተደረገላቸው 1 ሺ... read more
ኢሚግሬሽን ውስጥ የሚታየው ብልሹ አሰራርና መፍትሄው
https://youtu.be/df_HeM5X-Ws
read more
ማንቸስተር ዩናይትድ በአዲስ ባለሀብት እጅ ሊወድቅ መድረሱን ቱርኪ አል-ሼክ ፍንጭ ሰጡ
መስከረም 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሳዑዲ ዓረቢያ የስፖርት እና የመዝናኛ ባለሥልጣን እንዲሁም ታዋቂው የቦክስ ፕሮሞተር ቱርኪ አል-ሼክ የእንግሊዙን ታላቅ ክለብ ማንቸስተር... read more
የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት በተያዘው የበጀት ዓመት 9 አዳዲስ መርከቦችን እና ከ400 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎችን በግዢ እንደሚያስገባ አስታወቀ
መስከረም 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት የሃገር ውስጥና የውጭ ሸቀጦችን የምልልስ ሂደት ለማሳለጥ የአዋጭነት ጥናት አድርጎ ወደ ኢንቨስትመንት... read more
በኢትዮጵያ ባለፈው አመት ከ10ሺህ የሚበልጡ እናቶች በወሊድ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ
ይህ የተገለጸው የህጻናትና እናቶች ሞትን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ በተደረገበት መድረክ ላይ ነው።
በአንድ ከተማ መስተዳደር እና በ5 ክልሎች ይተገበራል በተባለው... read more
ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችል የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ
ኢትዮ ቴሌኮም ከጅማ ከተማ አስተዳደር ጋር በከተማዋ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የስማርት ሲቲ “ስማርት ጅማ” ፕሮጀክትን ለመተግበር የሚያስችል... read more
አካታች የትምህርት ፖሊሲዎች በወረቀት ላይ ቢኖሩም በተግባር እየተሰራባቸው አለመሆኑ ተገለጸ
ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አብርሆት ስፔሻላይዝድ የሳይኮሎጂ ማዕከል ከለርኒንግ ሊንክ አፍሪካ፣ ከኬንያታ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር... read more
ምላሽ ይስጡ