ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል አጀንዳ ለማሰባሰብ ክልሉን ወክለው ከሚንቀሳቀሱ ተቋማት ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም፣ እስካሁን የሚፈለገው ውጤት እንዳልመጣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል።
በክልሉ አስተማማኝ እና የተረጋጋ ሰላም ባለመኖሩ ምክንያት፣ እስካሁን በቦታው በአካል ተገኝቶ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወን እንዳልተቻለ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ሂደቱን ስኬታማ ለማድረግ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ከሕወሃት አመራር፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበራት፣ ከጋዜጠኞች እና ይመለከታቸዋል ከተባሉ ሌሎች ተቋማት ጋር ከ22 ጊዜ በላይ ተደጋጋሚ ውይይቶችን ቢያደርግም፤ እስካሁን ድረስ ወደ ተግባር መግባት የሚያስችል ውጤት አልተገኘም ብለዋል።
በዚህም ምክንያት ኮሚሽኑ የመጨረሻ አማራጭን በመጠቀም፣ በአዲስ አበባ ከተማ ከትግራይ ተወላጆች ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ ማከናወኑን ፕሮፌሰሩ አስታውሰዋል።
በውይይቱ ላይም በቀጥታ ከትግራይ ክልል የመጡ 300 ተሳታፊዎች እና በአዲስ አበባ የሚኖሩ 400 የክልሉ ተወላጆች በጥቅሉ 700 ሰዎች መሳተፋቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ ሁሉንም አካላት ያካተተ ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ በትግራይ ክልል ያለውን ተሳትፎ ለማረጋገጥ ሰፊ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱንም የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የዘለንስኪ ልፋት ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የቸለሰው የትራምፕ ውሳኔ
https://youtu.be/NqY57YAokwU?si=GTy9_t5Oo1uH5v3q
read more
አፕል የሲሪ (Siri) ረዳቱን በጎግል ጄሚናይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለማዘመን ከጎግል ጋር ስምምነት አደረገ
ጥር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቴክኖሎጂው ግዙፍ ኩባንያ አፕል ታዋቂውን የ"ሲሪ" (Siri) ድምፅ ረዳት አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ለማዘመን የጎግልን "ጄሚናይ"... read more
ከአህጉሪቱ ወሳኝ የ2063 አጀንዳዎች ሁሉ ሰላምና ጸጥታ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ተባለ
ከአህጉሪቱ ወሳኝ የ2063 አጀንዳዎች ሁሉ ሰላምና ጸጥታ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው ሲሉ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲሱ የህብረቱ ሊቀመንበር ጃኦ... read more
የመቶ አለቃ ካሳኤ የቤት ወራሽነት ውዝግብ እና የነዋሪዎች ቅሬታ
ሙሉ ፕሮግራሙን ለማዳመጥ ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ
ጉዳያችሁን ጉዳያችን አድርገን፣ እልባት ያገኝ ዘንድ መፍትሔ በምናፋልግበት የ"ሞግዚት" ጥንቅራችን ዛሬ አንድ ወቅታዊ ጉዳይን ልንመለከት... read more
ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ500 ሄክታር የደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ
ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አሥተዳደር የገጠር ቀበሌዎች በጣለው ከባድ በረዶ ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ... read more
ከቀውስ ቀጠናዎች እስከ ህልውና ፈተና፦ በኢትዮጵያ የስደተኞች የጤና፣ የመብት ከለላ እና የሰብዓዊ እርዳታ እጥረት አሳሳቢነት
በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በሚቀጥሉት ውጥረቶች፣ የሰላም እጦት እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በኢትዮጵያ መጠለያ ያገኙ ስደተኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገራቸው... read more
በኢትዮጵያ በመገኛ ቦታቸው ተለይተው የሚታወቁ ጥራት ያላቸው ምርቶች በመልክዓ ምድራዊ አመላካች ሥርዓት በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ ለማድረግ የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተገለፀ
አንድን ምርት የተመረተበት አካባቢ በሚሰጠው ጥራት ወይም ልዩ ባህሪ መሰረት አድርጎ ለሸማቾች እንደሚያቀርቡ ይታወቃል፡፡ በዘመናዊው የንግድ ስርዓት ውስጥም የተለያዩ ምርቶች... read more
ኢትዮጵያ በቅርቡ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የአቻ ግምገማ ሊታስደርግ እንደምትችል ተገለጸ
በየአመቱ የአፍሪካ ህበረት ጉባኤ ሲካሄድ በኔፓድ አስተባባሪነት የሚካሄደው የአቻ ሀገራት ግምገማ ተጠቃሽ ነው፡፡ በግምገማው ፈቃደኛ የሆኑ ሀገራት በመልካም አስተዳደር ፤... read more
አፍሪካ በተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ተጠየቀ
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ተጠይቋል።
የአፍሪካ ህብረት... read more
በልደታ ክ/ከተማ በተደረገ የሌባ ጥናት የተለያዩ የተሠረቁ የመኪና ዕቃዎችን ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር መያዙን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሌባ ተቀባዮች ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ የመኪና ዕቃዎችን በማከማቸት ዕቃዎቹን ለማስመለስ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠየቅባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ... read more
ምላሽ ይስጡ