ግንቦት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአየር ላይ የበላይነትን ለመጨበጥ የሚደረገው የልዕለ-ኃያላኑ ፍልሚያ ሌላ ምዕራፍ ይዟል። በወታደራዊ አቪዬሽን አለም ውስጥ ትልቅ መነጋገሪያ የሆነው የሩሲያው እጅግ ዘመናዊው Sukhoi Su-57 እና የአሜሪካው የቴክኖሎጂ ቁንጮ F-35 Lightning II ፍልሚያ የአየር ላይ ውጊያ ስትራቴጂን ሙሉ በሙሉ የቀየረ ሆኗል። ነገር ግን ብዙዎችን የሚያስገርመው አንድ ግዙፍ እውነታ አለ፦ የሩሲያ የጦር ጄቶች ከአሜሪካዎቹ በአካልም ሆነ በክብደት እጅግ በጣም የገዘፉና ግዙፍ የሆኑት ለምንድነው? ይህ ልዩነት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን ፍፁም የተለያየ ወታደራዊ ፍልስፍና ውጤት ነው ተብሏል!
የመጀመሪያውና ዋናው ምክንያት የሀገራቱ የቆዳ ስፋት እና የነዳጅ ፍላጎት ልዩነት ነው። ሩሲያ በቆዳ ስፋት የአለማችን ትልቋ ሀገር በመሆኗ፥ የሀገሪቱን ሰፊ ድንበር ለመጠበቅ የሩሲያ ጄቶች ያለ ነዳጅ መሙያ አውሮፕላን ረጅም ርቀት መጓዝ አለባቸው። Su-57 በውስጡ እጅግ በጣም ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ መያዝ እንዲችል ተደርጎ በመገንባቱ አውሮፕላኑ ግዙፍ ሊሆን ችሏል። በአንፃሩ አሜሪካ በየቀጠናው ባሏት የጦር ሰፈሮች እና የነዳጅ መሙያ አውሮፕላኖች ስለምትተማመን F-35ን በአነስተኛ መጠን መስራት መርጣለች።
ሌላው ምክንያት ደግሞ የሞተር ብዛት እና የፍጥነት ስትራቴጂ ነው። የሩሲያው Su-57 ሁለት ግዙፍ ሞተሮች (Twin-Engine) የታጠረ ሲሆን፥ ይህም እጅግ ፈጣን እና በአየር ላይ በቀላሉ የማይገመቱ አስደናቂ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ያስችለዋል። የአሜሪካው F-35 ግን በአንድ ሞተር (Single-Engine) ብቻ የሚሰራ በመሆኑ መጠኑ እንዲያንስ እና ለራዳር አስቸጋሪ እንዲሆን ረድቶታል።
በተጨማሪም Su-57 በውስጡ ግዙፍ የሆኑ ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን እና እጅግ ኃይለኛና ትላልቅ የራዳር ሲስተሞችን ይዞ ይጓዛል። አሜሪካውያን ግን “የማይታይነት” (Stealth) ቴክኖሎጂ ላይ ስላተኮሩ ሁሉንም ነገር አሳንሰውና ደብቀው ለመስራት መርጠዋል።
📌 ባጭሩ፡ የአሜሪካው F-35 ሳይታይ ቀድሞ የማጥቃት ስትራቴጂን ሲከተል፣ የሩሲያው Su-57 ግን በአካል ግዙፍ፣ ፈጣን እና በአየር ላይ በሚደረግ የፊት ለፊት ፍልሚያ (Dogfight) አይቀሬ በሆነ ኃይል ላይ ያተኮረ የምህንድስና ውጤት ነው ተብሏል።
የአየር ላይ የበላይነቱን ማን የሚወስደው ይመስልዎታል? ግዙፉ Su-57 ወይንስ ረቂቁ F-35?
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ