ግንቦት 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መተላለፍ ምክንያት የመራጮች ምዝገባ በታገደባቸው አካባቢዎች፣ በድምፅ መስጫው ዕለት የመራጮች ምዝገባ ተካሂዶ ሕዝቡ በምርጫው እንዲሳተፍ እንደሚደረግ አስታወቀ። ቦርዱ በተጨማሪም ለቅሬታና ጥቆማ ማቅረቢያ የሚሆን ነፃ የስልክ መስመር ማዘጋጀቱን ገልጿል።
የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ቦርዱ በድህረ-ምርጫ ወቅት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ከቦርዱ ሕግ ውጪ የመራጮች ምዝገባ ሲያከናውኑ የነበሩ በርካታ ምርጫ ጣቢያዎች በክትትልና በደረሱ ጥቆማዎች መሠረት በጊዜያዊነት እንዲታገዱ ተደርጓል።
ይሁን እንጂ በእነዚህ የታገዱ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎች የመምረጥ መብታቸው እንዳይጣስ ለማድረግ ልዩ ዝግጅት መደረጉን ዋና ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው የድምፅ መስጫ ዕለት፣ በእነዚሁ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በአንድ ላይ ተከናውኖ ሕዝቡ ቀጥታ በምርጫው እንዲሳተፍ ይደረጋል ብለዋል።
ለቅሬታ ማቅረቢያ “6214” የነፃ ስልክ መስመር ተዘጋጅቷል
ምርጫ ቦርድ የምርጫው ሂደት ግልጽና ፍትሐዊ እንዲሆን ለማገዝ፣ በምርጫው ዕለት ለሚያጋጥሙ ማንኛቸውም ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ማስተናገጃ የሚሆን 6214 የተሰኘ ነፃ የጥሪ መስመር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ያስታወቀ ሲሆን፣ ዜጎች በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዘቧቸውን ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና ቅሬታዎች ይህንን የነፃ ስልክ መስመር በመጠቀም እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በእስራኤልና በኢራን ጦርነት መቀስቀስ ምክንያት መስተጓጎል የገጠማቸው ጉዳዮች ምንድን ናቸው?
👉የነዳጅ ዋጋ መናር:ግጭቱ በነዳጅ ገበያው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል። ኢራን በዓለም የነዳጅ አቅርቦት ላይ ትልቅ ቦታ የምትይዝ ከመሆኗም በላይ የሆርሙዝ... read more
በጣሊያን የአውሮፕላን ሞተር ሰው ስቦ አስገባ
በጣሊያን አንድ ሰው በአውሮፕላን ሞተር ተስቦ በመግባቱ የተነሳ ሁሉም የቤርጋሞ አውሮፕላን ማረፊያ በረራዎች እንዲታገዱ ተደረገ
ሐምሌ 1 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሰሜናዊ ጣሊያን... read more
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት ጋር እያካሄደችው ያለው ግንኙነት የባህር በር ለማግኘት የተሻለ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ነው ተባለ
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር እያካሄደችው ያለው ግንኙነት የባህር በር ለማግኘት የተሻለ ዲፕሎማሲያዊ ሂደት መሆኑን አምባሳደሮችና... read more
በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ በመከሰቱ ምክንያት አስቸኳይ የኬሚካል ርጭት ሊካሄድ ነው
መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ፅህፈት ቤት በቀጠናው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን አስታወቀ። ፅህፈት... read more
ከዛሬ ጀምሮ ከ13 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ ነው ተባለ
ህፃናት ላይ የሚከሰተውን ፖሊዮ እና ተጓዳኝ በሽታዎችን ለመከላከል በዘመቻ መልክ የፖሊዮ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመናኸሪያ... read more
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የዚህ አመት ምዝገባ እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ የዚህ ዓመት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ምዝገባ... read more
👉ቆይታ ከቢኒያም በለጠ ጋር
በመናኸሪያ ሌማት ዝግጅት የመናኸሪያ እንግዳ ፕሮግራም
በመናኸሪያ እንግዳ ፕሮግራማችን #ከመቄዶኒያ የአዕምሮ ህሙማን እና የአረጋዊያን መርጃ መዕከል መስራች #ቢኒያም በለጠ እንግዳችን በመሆን... read more
ለአንድ ሃገር ዘላቂ ሰላም መስፈን ከሚያስፈለጉ ነገሮች መካከል በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ግንኙነት የጠነከረ እና ሰላማዊ መሆን እንዳለበት ይገለጻል፡፡
ቢሆንም ግን በሃገራችን ያለው የፖለቲካ ውቅር እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንኙነት ደካማ ሆኖ የቆየ መሆኑ ይነሳል።
ቢሆንም ግን ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ... read more
መርዛማ ብረቶችን በመመገብ ንፁህ ወርቅ የሚያመነጭ ባክቴሪያ ተገኘ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች መርዛማ ብረቶችን ከተመገበ በኋላ ንፁህ ወርቅ የማምረት ችሎታ ያለው ባክቴሪያ መለየታቸውን አስታወቁ። ይህ ግኝት በወርቅ... read more
በክልሉ በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የተሃድሶ ኮሚሽን ስልጠና ዳግም መጀመሩ ተገለጸ
በትግራይ ክልል ከ75,000 በላይ የሚገመቱ የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ የማስፈታትና በዘላቂነት ወደ መደበኛ ሕይወት ለማስገባት የታቀደው የተሃድሶ ሥልጠና በክልሉ በተፈጠረው የፖለቲካ... read more
ምላሽ ይስጡ