ግንቦት 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕግ መተላለፍ ምክንያት የመራጮች ምዝገባ በታገደባቸው አካባቢዎች፣ በድምፅ መስጫው ዕለት የመራጮች ምዝገባ ተካሂዶ ሕዝቡ በምርጫው እንዲሳተፍ እንደሚደረግ አስታወቀ። ቦርዱ በተጨማሪም ለቅሬታና ጥቆማ ማቅረቢያ የሚሆን ነፃ የስልክ መስመር ማዘጋጀቱን ገልጿል።
የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ቦርዱ በድህረ-ምርጫ ወቅት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ከቦርዱ ሕግ ውጪ የመራጮች ምዝገባ ሲያከናውኑ የነበሩ በርካታ ምርጫ ጣቢያዎች በክትትልና በደረሱ ጥቆማዎች መሠረት በጊዜያዊነት እንዲታገዱ ተደርጓል።
ይሁን እንጂ በእነዚህ የታገዱ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎች የመምረጥ መብታቸው እንዳይጣስ ለማድረግ ልዩ ዝግጅት መደረጉን ዋና ሰብሳቢዋ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው የድምፅ መስጫ ዕለት፣ በእነዚሁ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በአንድ ላይ ተከናውኖ ሕዝቡ ቀጥታ በምርጫው እንዲሳተፍ ይደረጋል ብለዋል።
ለቅሬታ ማቅረቢያ “6214” የነፃ ስልክ መስመር ተዘጋጅቷል
ምርጫ ቦርድ የምርጫው ሂደት ግልጽና ፍትሐዊ እንዲሆን ለማገዝ፣ በምርጫው ዕለት ለሚያጋጥሙ ማንኛቸውም ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ማስተናገጃ የሚሆን 6214 የተሰኘ ነፃ የጥሪ መስመር ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።
ቦርዱ ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ያስታወቀ ሲሆን፣ ዜጎች በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዘቧቸውን ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና ቅሬታዎች ይህንን የነፃ ስልክ መስመር በመጠቀም እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የሴቶች ያለዕድሜ ጋብቻ እና ግርዛት የወንጀል ህግ እንዲሻሻል ለፍትህ ሚኒስቴር የማሻሻያ ጥናት መቅረቡ ተገለጸ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ የተጣለው የወንጀል ቅጣት... read more
ቻይና ሰው ሰራሽ የሰው ልጅ ጽንስን(ሽል) ወደ ጠፈር ጣቢያዋ በመላክ ታሪካዊ ሙከራ አደረገች
ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሰውን ልጅ ወደ ማርስ እና ጨረቃ ለማጓጓዝ እንዲሁም በህዋ ላይ በቋሚነት ለማስፈር ለሚደረገው ጥረት ትልቅ... read more
ዳግም ምዝገባ እንዲያካሄዱ ጥሪ ከቀረበላቸው 102 ተቋማት መካከል 84 የሚሆኑት ምዝገባ ባለማካሄዳቸው እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ ተገለጸ
ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢፌዴሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን በ2017 ዓ.ም የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ስልጠና መስኮቻቸውን በአዲስ የፍቃድ... read more
ብልፅግና ፓርቲ በሚያካሄደው ውይይት ከሀገሪቱ ሰላም እና ደህንነት ባሻገር ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም በሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ... read more
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎች ዕድሜ ከሚታሰበው በላይ ረዘም ያለ መሆኑ ተረጋገጠ
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርቡ በጂኦታብ (Geotab) የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው፣ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎች የአፈጻጸም ቅናሽ ሳይታይባቸው እስከ 20... read more
“በውጭ እርዳታ ላይ ከመጠን በላይ ጥገኝ መሆን ሀገራዊ የቤት ሥራዎችን እያስተጓጎለ ነው” — ሲሲአርዲኤ (CCRDA)
ሰኔ 10 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍሪካ የሲቪል ማኅበራት ኅብረት (ሲሲአርዲኤ) ከውጭ በሚገኝ ዕርዳታ ላይ ከመጠን በላይ ጥገኝ መሆን ሀገራዊ የቤት... read more
በዲጂታል ዘርፍ ወጣቶችን ለማብቃትና ለማሰልጠን ዓላማ ያደረገው “አዶናይ ቲክቶክ አካዳሚ” ሊከፈት ነው
ሰኔ 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ወጣቶች በፍጥነት እየተለወጠ ያለውን የዲጂታል ዓለም በተሳካ ሁኔታ እንዲቀላቀሉና እንዲያሸንፉ ለማስቻል “አዶናይ ቲክቶክ አካዳሚ” ሥራ... read more
ኢትዮጵያ በግጭት አካባቢ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥበቃ እንዲደረግ የሚያዘውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ እንድትቀበል ግፊት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በግጭት አካባቢ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥበቃ እንዲደረግ የሚያዘውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ እንድትቀበል ግፊት እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር... read more
“ሚሳኤሎቻችን ባይኖሩ ኖሮ እንደ ጋዛ እንሆን ነበር” — የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ሀገራቸው የያዘችው የባሊስቲክ ሚሳኤል ፕሮግራም በፍፁም ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን በፅኑ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ... read more
“አንድም ሰው በሕይወት አይተርፍም!” — ኢራን ለአሜሪካ ያስተላለፈችው የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመካከለኛው ምስራቅ ለዓመታት ሲንተከተክ የቆየው ፍጥጫ አሁን ወደማይመለስበት እና እጅግ አደገኛ ወደሆነው ቀጥተኛ ጦርነት ምዕራፍ... read more
ምላሽ ይስጡ