ግንቦት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎቿን ባትጠቀም እንኳ፣ በሰዓታት ውስጥ የትኛውንም የዓለም ክፍል ማሽመድመድ የምትችልባቸው ግዙፍ ወታደራዊ አማራጮች እንዳሏት ይነገራል። ከአቶሚክ ቦምቦች በስተጀርባ ዋሽንግተን የምትመካባቸውና የዓለምን ኃይል ሚዛን የዘወሩት ዋነኛ አቅሞች ሲተነተኑም አስገራሚ ውጤቶች ታይተዋል።
አሜሪካ በዓለም ውቅያኖሶች ላይ የምታሰማራቸው የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች “ተንቀሳቃሽ የጦር ሰፈሮች” በመባል የሚታወቁ ሲሆን፣ አንዷ መርከብ ብቻ ከአነስተኛ አገራት አየር ኃይል የሚበልጡ ከ80 በላይ ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖችን ተሸክማ የጠላትን ደጃፍ የማንኳኳት አቅም አላት። ይህ ኃይል አሜሪካ የትኛውንም አገር በባህር ዳርቻው በኩል ለመቆለፍ የምትጠቀምበት ዋነኛ መሣሪያዋ ሆኖ ያገለግላል።
ከዚህም ባሻገር የአሜሪካ አየር ኃይል የራዳር እይታን ሰብረው የሚገቡ የ”ስውር ቴክኖሎጂ” ቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑትን F-22 እና F-35 የጦር አውሮፕላኖች እንዲሁም B-2 ቦምብ ጣዮችን የታጠቀ ሲሆን፣ እነዚህ አውሮፕላኖች ጠላት ሳያያቸው ቁልፍ የጦር ዕዞችን የማውደም ልዩ ብቃት አላቸው። በጠፈር ላይ የተዘረጋው የሳተላይት መረብ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በንቃት ከመከታተሉም በላይ፣ “ስማርት” ቦምቦች ኢላማቸውን ስንጥቅ ሳይስት እንዲመቱ ያደርጋል።
በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከ800 በላይ የጦር ሰፈሮቿ አማካኝነት አሜሪካ በየትኛውም የምድር ክፍል ጦርነት ቢነሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዙፍ ኃይል የማንቀሳቀስ ብቸኛ የሎጂስቲክስ አቅም ያላት አገር ናት። ከወታደራዊ ጥቃቱ ጎን ለጎንም የጠላትን የኢንተርኔት፣ የኤሌክትሪክ እና የባንክ ሥርዓት በሳይበር ጥቃት በማሽመድመድ አገራትን ያለ ጥይት ከጥቅም ውጭ የማድረግ ስልታዊ የበላይነት አላት ነው የተባለው።
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ የአሜሪካ እውነተኛ ጥንካሬ የኒውክሌር ክምችቷ ሳይሆን፣ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊተገበር የሚችለው ይህ ዘመናዊና ፈጣን የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ስብስቧ ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ክሪፕቶ ከረንሲን በኢትዮጵያ መተግበር የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ተገለጸ
ታኅሳስ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከወረቀት እና የሳንቲም ገንዘብ በተጨማሪ የዲጂታል ገንዘቦች የክፍያና ኢንቨስትመንት አማራጭ እየሆኑ እንዳሉ ይገለፃል፡፡
ሀገራት ከእነዚህ መገበያያ... read more
በኢትዮጵያ የአንበሳ ዝርያ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ
ጥር 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተለያየ ጊዜ በተደረገ ጥናት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የአንበሶች ቁጥር መቀነስ በዋነኝነት የመኖሪያ ቦታቸው መጥፋት እንደሆነ... read more
በሰራተኞች አድማ ምክንያት አየር መንገዱ በረራዎቹን ለጊዜው አቋረጠ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የካናዳ አየር መንገድ(Air Canada)በአድማ ላይ ያሉ የበረራ አስተናጋጆች ወደ ስራ እንዲመለሱ የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ባለመቀበላቸው... read more
የሺዎችን ሕይወት የሚታደጉት የባቡር ሀዲድ ድንጋዮች አስገራሚ ምስጢር
ጥቅምት 26 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) በየቀኑ የባቡር ሀዲዶችን ስንመለከት፣ በሀዲዶቹ ሥር እና ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ የተሰባበሩ ሻካራ ድንጋዮች... read more
በአንድ ፈተና የሚወሰን ዕድል፦ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቻይና ተማሪዎችን እንቅልፍ የነሳው “ጋኦካኦ”
መጋቢት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና የሚገኙ ተማሪዎች ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብሔራዊ ፈተና ወይም "ጋኦካኦ" (Gaokao) የሚያደርጉትን እጅግ አድካሚ ዝግጅት... read more
በዘንድሮ በጀት ዓመት ለማዳበሪያ ግዢ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር መመደቡን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ
አገልግሎቱ ይህን ያለው ትላንት ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ለዘንድሮ የምርት ዘመን የሚገዛው የማዳበሪያ መጠን ካለፈው ዓመት አንጻር የ4... read more
ውጥረት ያስነሳው አዲስ የባህር ወሽመጥ ስም ጥያቄ በኒው ጀርሲ ሪፐብሊካን
ሰኔ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኒው ጀርሲ ግዛት የሚገኝ አንድ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል፣ የዴላዌር ቤይን "የኒው ጀርሲ ወሽመጥ" (The Bay... read more
ብልፅግና ፓርቲ በሚያካሄደው ውይይት ከሀገሪቱ ሰላም እና ደህንነት ባሻገር ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማጠናከር ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትላንት ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም በሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ... read more
ድምፃዊ ዓምደ-ገብርኤል አድማሱ አዲሱን “ወሄነት” የሚል መጠሪያ ያለውን ሶስተኛ አልበሙን የፊታችን እሁድ ለሙዚቃ አፍቃርያን ሊያቀርብ ነው
ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከአሁን በፊት "ሰበበር ኤነዌ" እና "ሟን ያትገፍሬ" በተሰኙት ሁለት የጉራጌኛ አልበሞቹ እንዲሁም በተለየ መልኩ "እያ ኧረሙድን... read more
💻 በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ የሚገኘው ያበጠው ሲሊንደር ሚስጥር፤ ለጌጥ ወይስ ለደህንነት? 🔌
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በላፕቶፕ እና ስልክ ቻርጀር ገመዶች ላይ ወደ ጫፉ አካባቢ ያበጠ ክብ ሲሊንደር ነገር አስተውለው ያውቃሉ?... read more
ምላሽ ይስጡ