ጥቅምት 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በፕሪሚየር ሊግ የውድድር ወርኅ ጥቅምት ምርጥ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች መመረጣቸው ታውቋል። የብሬንትፎርዱ ክንፍ አጥቂ ብሪያን ምቤሙ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ሲመረጥ፣ የስፖርቲንግ ሊዝበኑ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ደግሞ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው መመረጣቸው ታውቋል።
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸውን ውጤት ባለማጣት እና በአጨዋወት መስመር ላይ በሚያደርጉት ጽኑ ጥረት—በወርኀ ጥቅምት ባስመዘገቡት ስኬት ለዚህ ክብር በቅተዋል። ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ቡድኑን በወርኀ ጥቅምት በተከታታይ በፕሪሚየር ሊጉ ድል እንዲቀዳጅ በማድረጋቸው ተመርጠዋል።
ይህ ምርጫ አሞሪምን ከኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶ፣ ጆዜ ሞሪንሆ፣ አንድሬ ቪያስ ቦአስ፣ ብሩኖ ላዥ እና ቪቶር ፔሬራ በመቀጠል የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ክብርን ያገኘ ስድስተኛው ፖርቹጋላዊ ያደርገዋል። አሰልጣኙ፣ “በግሌ ያሳካሁት ነገር የለም፤ የተጫዋቾቼ እና የአሰልጣኞች አባላት የጋራ ውጤት ነው” ሲሉ፣ ቀጣይ ግባቸውም የሚቀጥለውን ወር ማሳካት መሆኑን ገልጸዋል።
የካሜሮናዊው የብሬንትፎርድ ክንፍ አጥቂ ብሪያን ምቤሙ የወሩ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አግኝቷል። ለዚህ ክብር ያበቁት በወርኀ ጥቅምት ወር አስመዝግቧቸው የነበሩት ወሳኝ ጎሎች ናቸው። በወሩ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ያስቆጠራቸው ጎሎች፣ በተለይም ሊቨርፑል ላይ ጨዋታው በተጀመረ በ62 ሰከንድ ውስጥ ያስቆጠራት ፈጣን ጎል እንዲሁም ብራይተንን 4-2 ሲረቱ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ተጠቃሽ ናቸው።
የወርኀ ጥቅምት ምርጥ ጎል የአስቶን ቪላው ኤሚሊያኖ ቡዌንዲያ ቶተንሃምን 2-1 በሆነ ውጤት በረቱበት የ8ኛ ሳምንት ጨዋታ ላይ ያስቆጠራት ጎል ሆና ተመርጣለች።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ