ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቻይና ለጠፈር ምርምር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሌላ አስደናቂ እርምጃ ወስዳለች። የቻይና የጠፈር መርሃ ግብር (China’s space program) በቲያንጎንግ የጠፈር ጣቢያ ላይ ልዩ ንድፍ ያለውና ጭስ የማያወጣ ምድጃ በተሳካ ሁኔታ አሰማርቷል። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ በጠፈር ላይ ለረጅም ጊዜ ለሚቆዩ ጠፈርተኞች ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሏል።
ይህ ምድጃ፣ ቀደም ሲል በጠፈር ላይ ከነበሩት ምግብ ማሞቂያ መሳሪያዎች በተለየ እስከ 190 የሚደርስ የሙቀት መጠን ማመንጨት ይችላል። ይህም ጠፈርተኞች ቀደም ሲል ከነበራቸው ቀላል የማሞቅ ሂደት አልፈው ትኩስ ምግብ እንዲያበስሉ አስችሏቸዋል ነው የተባለው።
በዜሮ ስበት አካባቢ ጭስ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል፣ ምድጃው ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም በሚችል ካታሊሲስ እና ባለ ብዙ ሽፋን ማጣሪያ (filtration) ዘዴ ተደግፏል። ይህም ምግብ በሚበስልበት ጊዜ ምንም አይነት ጭስ ወይም ሽታ እንዳይኖር በማድረግ በጠፈር ጣቢያው ውስጥ ደህንነቱ የተጠበቀ አሠራርን ያረጋግጣል ነው የተባለው።
በዚህ አዲስ ምድጃ አማካኝነት ቻይናውያን ጠፈርተኞች እንደ የዶሮ ክንፍ እና ስቴክ የመሳሰሉ ምግቦችን በጠፈር ላይ ማዘጋጀት ችለዋል። ለምሳሌ የዶሮ ክንፎችን ለማብሰል የተጠቀሙበት ጊዜ 28 ደቂቃ አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ ፈጠራ ለጠፈርተኞች የምግብ አማራጮችን በማብዛት ለረጅም ጊዜ በሚደረጉ ተልዕኮዎች ወቅት የኑሮ ጥራትን እና የስነ-ልቦና ጤንነትን ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ