መስከረም 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ ማንኛውንም ተሸከርካሪ ባለማቆም ወላጆች ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ የትምህርት መጀመርን ተከትሎ ከወትሮው በተለየ መልኩ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ እንደሚስተዋል የሚናገሩት በባለስልጣኑ የትራፊክ ቁጥጥር እና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አያሌው አቲሳ፤ ወላጆች በየትኛውም መልኩ በትምህርት ቤት ዙሪያ ተሸከርካሪ ባለማቆም ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ወላጆች በተሸከርካሪ መንገድ ላይ ለሰከንዶች ተማሪዎችን ማውረድ እንደሚችሉ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ተሽርካሪያቸውን ለደቂቃዎች በስፍራው ማቆምም ሆነ አቁሞ መውረድ እንደማይቻል አስታውቀዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጥብቅ የቁጥጥር ሥራ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
ባለፉት 3 ወራት ነዋሪዎች የትራንስፖርት እጥረት እንዳይገጥማቸው በተለያየ ምክንያት ተበላሽተው ለዓመታት ከአገልግሎት ውጪ የነበሩ ባሶች እና በግል የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽርካሪዎችን ከባለንብረቶች ጋር በመነጋገር ጥገና እንዲደረግላቸውና ወደ ስራ እንዲመለሱ መደረጉን ደግሞ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የትራንስፖርት ስምሪት መከለሱን ያስታወቁት ኃላፊው፤ ቢሮው ከሰጠው ስምሪት ውጪ መንቀሳቀስም ሆነ መቆም እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ የሚፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ ችግር ለመቀነስ፤ በቀጣይ የሚተገበሩ የመፍትሄ አማራጮች መኖራውን የገለጹት ሃላፊው፤ ወላጆች ወደ ት/ት ቤት ግቢ በመግባት ተማሪዎችን እንዲያወርዱ እና እንዲጭኑ ጠይቀዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ