ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ራሱን ልዩ ሰው ወይም The Special one እያለ የሚጠራው ፖርቹጋላዊው አወዛጋቢ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ ጋር ያላቸው እህል ውሀ አብቅቷል።
በፈረንጆቹ ሚሊኒየም የጀመረው የሞሪንሆ የአሰልጣኝነት ጉዞ እስከ 2020 ድረስ ታላቅ ገድሎችን በመፈጸም ወርቃማ ስኬቶችን በተለያዩ ክለቦች ማስመዝገብ ችሏል።
የቀድሞ የቤኔፊካ ፤የፖርቶ ፤ የቼልሲ ፤ የሪያል ማድሪድ ፤ የኢንተርሚላን ፤ የሮማ ፤ የማንቸስተር ዩናይትድ እና የቶተንሀም አሰልጣኝ በመሆን የተለያዩ የዋንጫ ክብሮችን ማሳካት የቻለው ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ፌነርባቼን አምና በቱርክ ሱፐር ሊግ 2ኛ ደረጃን ይዘው እንዲያጠናቅቁ ማስቻሉ ይታወሳል።
ዘንድሮ የቱርኩ ክለብ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለማለፍ ከቤኔፊካ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በመሸነፉቸው እና ቡድኑ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሳይሆን የዩሮፓ ሊግ እንደሚሳተፉ መረጋገጡን የ62 አመቱ ፖርቹጋላዊ ከፌነርባቼ ጋር መለያየታቸው ዋነኛው መንስኤ እና ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።
ምላሽ ይስጡ