ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት አመት 162 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ማስታወቁ ይታወሳል።
በ2018 በጀት አመት በገጠርና በከተማ የቴሌኮም ማስፋፊያ በመስራት የደንበኞቹን ቁጥር አሁን ካለበት 83 ነጥብ 2 ሚሊየን ወደ 88 ሚሊየን ለማድረስ ይሰራል ሲሉ የገለፁት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ናቸው።
ተቋሙ በአዲሱ በጀት ዓመት 2 መቶ 35 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰዋል።
በትዕግስት ተስፋየ
ምላሽ ይስጡ