ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በከተማዋ የሰራተኛ ደመወዝ ግብር የማይከፍሉ የተለያዩ ሀገራት ኤንባሲዎች ወደ ክፍያ ስርዓት እንዲገቡ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ2017 ዓ.ም በ14 ዘርፎች ላይ ጥናት በማድረግ ወደ ግብር ስርአቱ የማምጣት ስራ መጀመሩን የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ ሁሉም ሳይሆኑ አንዳንድ በህንፃዎች ውስጥ የሚሰሩ ነጋዴዎች፤ ሪልስቴቶች ፤ኤንባሲዎች፤እና ሌሎችም የስራ ዘርፎች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ ግን ወደ ታክስ ስርአቱ ያልገቡ መኖራቸውን በማስታወስ በዚህ አመት በተደረገው ማሻሻያ በተሰበሰበው የገቢ ግብር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን አመላክተዋል፡፡
ቢሮው ፍትሃዊ የገበያ አሰባሰብ እንዲኖር የተመዘገቡት እንዲሁም ግብር ለመክፍል ያልተመዘገቡት አካላት እንዲካተቱ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በከተማዋ በኮሪደር ልማት ከመኖሪያቸው ተነስተው ወደ ሚገኙበት ስፍራ በርካታ ግብር ለመክፍል ያልተመዘገቡ ነጋዴዎች መኖራቸውን በመግለፅ በቀጣይ ሁሉንም ለማካተት በትኩረት እንደሚሰራም ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ 350 ቢሊዬን ብር ግብር ለመሰብሰብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡
ምላሽ ይስጡ