ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) – በ2017 በጀት ዓመት ከ1ሺሕ በላይ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮችን ማጣራቱን የህገ-መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
ለጉባኤው በበጀት አመቱ 1ሺሕ 660 ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች እንዲጣሩ መቅረባቸውን የጉባኤው የኮሙኒኬሽንና የቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ይርጋለም ጥላሁን ተናግረዋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 1ሺሕ 443 የሚሆኑት ምንም አይነት የህገመንግስት ጥሰት የሌለባቸው በመሆናቸው የውሳኔ ግልባጭ እንዲጣራላቸው ላቀረቡ ሰዎች መሰጠቱን ያነሱት ዳይሬክተሯ፤ 31 የሚሆኑት ህገ መንግስታዊ ትርጉም የሚያስፈልጋቸው በሚል ለምክር ቤት መላካቸውንና 29 ጉዳዮች ደግሞ በተለያየ ምክንያት እንደተቋረጡ እንዲሁም፤ ሌሎች ተጨማሪ መረጃን የሚፈልጉ ጉዳዮችን ላይ ተጨማሪ መረጃን በማሰባሰብ ጥናት እየተደረገ እንደሆነ ዳይሬክተሯ ገልፀዋል፡፡
ክሳቸውን ያቋረጡ አቤቱታ አቅራቢዎች በራሳቸው ፍላጎት እንደሆነና የተቋረጡ ጉዳዮችም በድጋሚ ይታልን ተብለው ለጉባኤው ከቀረቡ እንደሚታዩም ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ በፊት ለመጣራት በሚቀርቡ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች የጊዜ ገደብ እንዳልነበራቸውና አሁነን ላይ ለመጣራት የሚቀርቡ ጉዳዮች በሦስት ወር ውስጥ ለጉባኤው መቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ምንም እንኳን ለተቋሙ ዋነኛ የሚባለው ህገመንግስታዊ ጉዳዮችን የሚመለከት ይዘት ያላቸው አቤቱታዎች በብዛት እየመጡ ባይሆንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አቤቱታዎች ግን ለጉባኤው እየቀረቡ እንደሆነ ነው የጉባኤው የኮሚኒኬሽንና የቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ይርጋለም ጥላሁን ያመላከቱት፡፡
ምላሽ ይስጡ