ሐምሌ 1 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ማዕከላዊ ክፍል በሚገኝ አንድ የቴሌኮም ኢጅፕት ሕንፃ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ አራት ሰራተኞች ህይወታቸው አልፎ 26 ሰዎች መቁሰላቸው ተዘገበ።
የእሳት አደጋው ዛሬ ማለዳ ላይ በሕንፃው ውስጥ ተከስቶ በፍጥነት መስፋፋቱን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የእሳት አደጋው መንስኤ እስካሁን በይፋ ያልተገለጸ ቢሆንም፣ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ታውቋል።
የካይሮ የእሳት አደጋና የድንገተኛ አደጋ ቡድኖች ወደ ስፍራው በመድረስ እሳቱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን እና ቆስለው የተገኙ ሰዎችን ወደ ሆስፒታሎች ማጓጓዝ እንደቻሉ የግብፅ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከተጎጂዎች መካከል አንዳንዶቹ በጢስ መታፈን ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በእሳት ቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ይህ አደጋ በቴሌኮም ኢጅፕት ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በግብፅ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል ነው የተባለው።
ምላሽ ይስጡ