በዩኒቨርስቲዎች የሚሰጠው የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) እንደገለጹት ፈተናው የሚሰጠው በ51 ዩኒቨርስቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ነው።
በዚህ ዓመት በሚሰጠው የመውጫ ፈተና 190,787 ቅድመ መደበኛ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ እና ከዚህም ውስጥ 102 ሺሕ 360 ተማሪዎች ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ፈተናው በ238 የትምህርት መርሃ ግብሮች በሁሉም የፈተና መስጫ ማዕከላት በበይነ መረብ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ ጨምረው ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ