ይህ የተገለጸው የህጻናትና እናቶች ሞትን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ በተደረገበት መድረክ ላይ ነው።
በአንድ ከተማ መስተዳደር እና በ5 ክልሎች ይተገበራል በተባለው ፕሮጀክት ከ1 ሚሊየን በላይ እናቶችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገልጿል።
በፕሮጀክቱ የቤተሰብ እቅድ፤ የጨቅላ ህጻናት ሞትና በወሊድ ምክንያት በሚያጋጥም የደም መፍሰስ የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር ለመቀነስ እንደሚሰራ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱን በይፋ ያስጀመሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በሀገሪቱ የእናቶች እና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጽ ከቅርብ አመታት ወዲህ በወሊድ ወቅት በሚያጋጥም የደም መፍሰስ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን አስታውቀዋል።
አሁን ያለው ቁጥር በ2030 በእጥፍ እንዲቀንስ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ለፕሮጀክቱ 16 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ መደረጉ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ በሲዳማ፤ በኦሮሚያ፤ በአማራ፤ በደቡብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ፕሮጅክቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው።
አጠቃላይ ከ400 መቶ በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች በሚገኙ 300 የተመረጡ የጤና ተቋማት ለመድረስ መታቀዱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ፕሮጀክቱ በቀጣይ 4 አመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎችም ለመድረስ እንደሚሰራ ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ