ሚያዚያ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና እና አሜሪካ መካከል የተስተዋለው ቀጣይነት ያለው ቀረጥ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ ላይ የተወሰነ ተጽዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል ተገምቷል።
ምክንያቱ ደግሞ ከቀረጡ በኋላ በሁለቱ አገራት መካከል አነስተኛ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ ሊስተዋል ይችላል የሚለው ነው።
እ.ኤ.አ. በ2025 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በአለም አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር በ29 በመቶ ጨምሮ፣ 4.1 ሚሊዮን ሽያጭ መከናወኑን አለም አቀፉ የገበያ ጥናት ድርጅት Rho Motion ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
በተጠቀሰው ጊዜ በቻይና 2.4 ሚሊዮን ሽያጭ ፣ በአውሮፓ 900ሺ ፣ በሰሜን አሜሪካ 500ሺ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች 300ሺሕ ተከናውኗል። ቻይና ከጠቅላላው ሽያጭ የ58 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻን ይዛለች።
በመጋቢት ወር ብቻ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በቻይና ገበያ መሸጣቸውን ተከትሎ በአገሪቱ ያለው የሽያጭ መጠን በ36 በመቶ ጨምሯል።
አሁን በቻይና እና አሜሪካ መካከል እየተስተዋለ ያለው ቀረጥ፣ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በኤሌክትሪክ ተሽከርካ ሽያጭ ላይ የተወሰነ ተጽእኖ ይኖረዋል፣ ምክንያቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል ሊኖር ይችላል ተብሎ የሚገመተው የሽያጭ መጠን ይቀንሳል ሲል የገበያ ጥናት ድርጅቱ መረጃ አመላክቷል።
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የነበረው የሽያጭ መጠን በ16 በመቶ ጨምሯል። እ.ኤ.አ. በ2024 በአሜሪካ ገበያ ከተሸጡ ተሽከርካሪዎች 60 በመቶ የሚሆኑት በአገር ውስጥ የተመረቱ ሲሆኑ ፣ የተቀሩት አብዛኛዎቹ የጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ እና ሜክሲኮ ምርቶች ናቸው።
በአውሮፓ የዘርፉ ግብይት በ27 በመቶ ጨምሯል ያለው የአናዶሉ ዘገባ፣ በሌሎች በርካታ አገራትም በተመሣሣይ ጭማሪ ማሣየቱን ገልጿል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 radio 99.1
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ