ታላቁ የኢትየጵያ ህዳሴ ግድብ የዛሬውን ትውልድ ከታሪክ ተወቃሽነት ያዳነ የጋራ አሻራችን ነው ሲሉ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳ ተናግረዋል ።
አባቶቻችን በአንድነት የአድዋን ድል እንደተጎናጸፉ ሁሉ የህዳሴ ግድቡ፣ ኢትዮጵያዊያን የአይቻልምን አስተሳስብ በጋራ ድል የነሱበት ነው ብለዋል።
አክለውም ግድቡ ሲጠናቀቅ ከሚያስገኘው የምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታ ባሻገር የሀገሪቱ ግምባር ቀደም የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ባህል፤ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የታላቁን የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የመሰረተ ድንጋይ የተጣለበትን 14ኛ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ‹‹ኢትዮጵያ ትችላለች›› በሚል መሪ ቃል የኪነ ጥበብ ዝግጅት ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ምላሽ ይስጡ