በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ሸታ ቀጠና (ካምፕ ሰፈር) ቁልቁለት በመውረድ ላይ እያለ በደረሰው ድንገተኛ ትራፊክ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡
አደጋው የደረሰው ቦንጋ ከተማ ገራዥ ጥገና (ሰርቪስ) ስደረግ የነበረው ኮድ(3) ታርጋ ቁጥር ደ/ም 013 26 የሆነው የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ መኪና ዛሬ ከቀኑ 10:30 ሰዓት አከባቢ ቼክ ለማድረግ መንገድ ላይ ይዘው በወጡበት ባጋጠመው ቴክኒክ ችግር መንገድ ጥሶ ሰው ቤት በመግባት ንብረት ላይ፤ከሁለቱ መካኒኮች በአንዱ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃ የሞተ ሰው አለመኖሩን የካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ምላሽ ይስጡ