የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎች ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየተነሱ መሆኑን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተለያዩ ጥናቶችን እያስደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ተረፈ በዳዳ አሁንም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች የማንነት ጥያቄዎቻቸው እንዲመለሱላቸው የሚጠይቁ አካላት ስለመኖራቸው ነው የሚያነሱት፡፡
ይሁን እንጂ ዜጎች ጥያቄዎቻቸውን ማንሳት ስለቻሉ ብቻ ምላሽ ያገኛሉ ተብሎ እንደማይጠበቅም ዳይሬክተሩ አጽዕኖት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ዜጎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ በህገ-መንግስቱ መሰረት ሊያሟላቸው እና ሊታዩላቸው የሚገቡ ጉዳዮችም እንዳሉ አብራርተዋል፡፡
ይሁን እንጂ ፌድሬሽን ምክር ቤቱ የማንነት ጥያቄዎችን በተመለከተ ጥናቶች እንዲደረጉ እያደረገ መሆኑን እና ወደ መጠናቀቂያዉ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ከዚህ ቀደም በሰራው ዘገባ በሀገሪቱ ከማንነትና ወሰን ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ሙሉ ለሙሉ ምላሽ አለማገኘታቸውን ተከትሎ በተለያዩ ጊዜያት እንዲሁም ወቅቶችን ተከትሎ በግጭት አዙሪት ውስጥ እንድንገባ የሚያደርጉን ጉዳዮች በመሆናቸዉ ደረጃ በደረጃ የጥናቱን ዉጤት መነሻ በማድረግ ምላሽ እንደሚሰጥባቸዉ ተጠቁሞ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ምላሽ ይስጡ