የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚገኙ አካላት ህጋዊ ግብይት እንዲፈፅሙ ለማስቻል ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት እስካሁን 1 ሺህ 145 የሚደርሱ በደረሰኝ ግብይት ያልፈጸሙ ነጋዴዎች ላይ እርምጀ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡
በቢሮ በኩልም የሚነሱ የስነ-ምግባር ችግሮችን ለመፍታት አዳዲስ ባለሙያዎችንም እንዲሰማሩ መደረጉን አንስተዋል፡፡ በዚህም መሰረት 58 በሚደርሱ የንግድ ቀጠናዎች ላይ በቡድን በማዋቀር እና አስተባባሪዎችን በመመደብ ቁጥጥር እያደረጉ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
ደረሰኝ መቁረጥ በንግዱ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን አገልግሎት ሰጪ በሆኑ ተቋማትም ጭምር ግዴታ በመሆኑ በባለሙያዎች ድንገተኛ ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ገልፀዋል፡፡
ለዚህም በምክትል ከንቲባ የሚመራ ግብረሃይል መቋቋሙን እና የተለያዩ የሚመለከታቸው አካላት የያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በከተማዋ በሚደረጉ ግብይቶች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የሚደረጉ የደረሰኝ ቁጥጥሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ