ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ቼልሲ ሁሉ አማረሽ ይመስል የተጫዋቾች አቅም ፤ ክህሎት ከአሰልጣኙ ፍልስፍና ጋር ተጣጥሞ ይሄዳል ወይ ፤ ተጫዋቹ ዘለቄታዊ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ማረጋገጫ አላቸው ወይ ፤ የቀድሞ ታሪኩን አጥንተው ነው ወይ ተጫዋች የሚያስፈርሙት ይሄ ሁሉ ጥያቄ ምልክት የሚነሳበት ጉዳይ ነው።
የቼልሲ የተጫዋቾች ግዢ እና ሽያጭ ፖሊሲ አወዛጋቢነቱ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ይህ ተጫዋች ማለትም ሬናቶ ቬይጋ ባሳለፍነው ክረምት ወር መስኮት ላይ ባዜልን በመልቀቅ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ የተቀላቀለው።
ተጫዋቹ ሁለገብ ተጫዋች ነው። ይህ ፖርቹጋላዊ በቀኝም በግራም ተመላላሽ የተከላካይ ስፍራ ቦታ እንዲሁም የመሀል ተከላካይ ስፍራ ቦታ ላይም ተሰልፎ መጫወት ይችላል።
21አመቱ ላይ ነው የሚገኘው ይህ ፖርቹጋላዊ የቼልሲ ቆይታው አሁን አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ቤን ቺልዌል ሁነኛ ተተኪ የመሆን አቅም እንዳለውም ታምኖበት ነበር ስታም ፎርድ ብሪጅ የደረሰው። አሁን ግን ክለቡ ለሱ በሚሰጡት የጨዋታ ጊዜ ማነስ እና የመሰለፍ ውስንነት ደስተኛ አለመሆኑ ሲገለፆ ቆይቷል።
ሜትር ከ 93 ስለሚረዝም ለቡድን የቆመ ኳስ የመከላከል ጥራትም ትልቅ ሚና እንደሚወጣ ይገመታል። ለፖርቹጋል 21 አመት በታች ቡድን ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ለሚሰለጥነው ዋናው ቡድንም ጥሪ ደርጎለት በአውሮፓ ዋንጫ እና ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ሀገሩን መወከል ችሏል።
ከስፖርቲንግ ሊዝበን ወደ ባዜል ወደ 4.6 ሚሊዮን ዩሮ ወጥቶበት ካቀና በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በድምሩ 26 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል። ዘንድሮ ግን በአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ስር የመሰለፍ እድልን በማጣቱ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ አሳውቋል ተብሏል። የጀርመኑ ክለብ ዶርትሙንድ ደግሞ የተጫዋቹ ጥብቅ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል።
ተጫዋቹ የመሀል ተከላካይ መስመር ተጫዋችም ሆኖ መጫወት እየቻለ ዌስሊ ፎፋና ጉዳት ሲያጋጥመው ለምን የመሰለፍ እድል አልተሰጠኝም የሚለው ጥያቄው በአሰልጣኙ አልተወደደሕ ተብሏል።
አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ተጫዋቹን አውሬቼዋለሁ ለሱ ያረኩለትን ነገር በሚገባ ያውቃል እሱ የሚያስፈልገን ቦታ ላይ ነው ሊያገለግለን የሚችለው ጉዳዩ ይኸው ነው ሲል ተደምጧል።
ታዲያ በክረምት 14 ሚሊዮን ፓውንድ ወጥቶበት ለ7 አመት በሰትታም ፎርድ ብሪጅ ለመቆየት ተስማምቶ ፊርማውን ያስቀመጠው ተጫዋች አሁን ክለቡን ለመልቀቅ ከጫፍ መድረሱ በብዙ እያስገረመም እያነጋገረም ይገኛል። ቼልሲ ቋሚ ዝውውር ነው የሚፈልጉት ለተጫዋቹ ደግሞ 30 ሚሊዮን ዩሮ እየጠየቁ ይገኛሉ። ወጥነት ባለው መልኩ 2 ጨዋታ እንኳን ላልተጫወተ ተጫዋች በ14 ተገዝቶ በ30 ሚሊዮን ዩሮ ለመሸጥ ማሰብ ምን የሚሉት ቀልድ ነው የብዙዎች ሀሳብ ነው። ዶርትሙንዶች ተደራድረው ተጫዋቹን የግላቸው ማድረጋቸው እንደማይቀር የእንግሊዝ ዜና አውታር የሆነው Daily mail በዘገባው ላይ አመላክቷል።
በሚካኤል ደጀኔ
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅ https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ https://youtube.com/@menahriaradio99.1?si=dRLPxb2AKvsMaph-
ምላሽ ይስጡ