ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ የፋይናንስ ምንጮችና ከካርበን የግብይት ሥርዓት የምታገኘውን ገቢ ማሳደግ የሚያስችላት የተሻሻለ ረቂቅ አዋጅ መጽደቁ ነው የተገለጸው፡፡
ኢትዮጵያ በደን ዘርፉ ከልማት አጋሮችና ከሌሎች አለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ምንጮችና ከካርበን ግብይት ስርዓት የምታገኘውን ድጋፍና ጥቅም ለማሳደግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መሆኑን የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ተናግረዋል፡፡
የሀገር ውስጥ አቅምን አሟጦ ለመጠቀምና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአየር ንብረት ለውጥ የሚደረጉ ድጋፎችን ማግኘት የሚያስችል አዋጅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በተሻሻለው አዋጅም በሃገራችን የተጎሳቆሉ አካባቢዎች በደን ልማትና በጥምር ደን ግብርና መልሰው እንዲያገግሙ ማድረግ፤ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ስነ-ምህዳራዊ ጠቀሜታ የሚሰጥ በመሆኑ በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉና ወደፊትም የሚተከሉ ችግኞችን ቀጣይነት ባለው መልኩ በፌደራል መንግስት የበጀት ድጋፍ የሚደረግለት እንደሆነ ሰብሳቢው አመላክተዋል፡፡
ክልሎችም የበኩላቸውን አስተዋፆ ማድረግ በሚያስችላቸው መልኩ መንግስትን መደፍ እንደሚገባቸው የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ