ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቤት ልማት ተደራሽነትን ለማስፋት የፋይናንስ አማራጭ ጥናቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።
በቅርቡ የሪል ስቴት አዋጅ መጽደቅን ተከትሎ ለቤት ተደራሽነት አማራጭ የፋይናንስ ጥናት እየተደረገ ስለመሆኑ ተገልጾ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ የጥናቱ ባለቤት ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ቢሆንም ጥናቱን የሚያከናዉነዉ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እንደሆነ ታዉቋል፡፡
አሁን ላይ ጥናቱ በቴክኒክ ደረጃ በርካታ ግብዓቶችን አካቶ መጠናቀቁን በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ተመራማሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ጥላሁን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። የቤት ፋይናንስን በሚመለከት ከአቅርቦትም ከፍላጎትም አንጻር ጥናቱ በጥልቀት እንደተመለከቱትና ባለድርሻ አካላት ስለሚኖራቸው ሚናና ሃላፊነትም በጥናቱ መካተቱን ተመራማሪው ገልጸዋል።
በተለይም ጥናቱ መዋቅራዊ ሂደትን በግልጽ በማስቀመጥና የህግ ክፍተትን ከመሙላት አንጻር ሁነኛ ማዕቀፎችን የያዘ ስለመሆኑ ተመራማሪው ገልጸዋል። አማራጭ የተባለው ፋይናንስ በማንና እንዴት የሚሉት ጉዳዮች ከፍላጎት አንጻር በግልጽ የተቀመጡ መሆናቸውንም በመጥቀስ አዋጁ ሲጸድቅ እራሱን ችሎ በቦርድ የሚተዳደር አሰራር እንዲኖረውም በጥናቱ ስለመመላከቱ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ለተጨማሪ ግብዓት በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ ባለድርሻ የሚባሉ አካላት ምክረ-ሃሳብ እንዲሰጡበት እንደሚደረግም ተመራማሪው አክለው ተናግረዋል። አሁን ላይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሂደቱ ተጠናቆ ይፋ እንዲደረግ ለማድረግ ከሚመለከተው ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጋር ሆነው እየሰሩ እንዳሉም አቶ ሰለሞን አብራርተዋል።
የቤት ልማት ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚረዳ የቤት ፋይናንስ አማራጭ ጥናት አጥንቶ ማቅረብ በዘርፉ ያሉ አቤቱታዎችንና ክፍተቶችን እንደሚሞላ ከአሁን ቀደም በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርም መገለጹ ይታወሳል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ