![](https://menahriaradio.com/storage/2024/12/ከቅመማ-ቅመም-ምርት-ከ3-ሚሊዮን-ዶላር-በላይ-ገቢ-መገኘቱ-ተገለጸ-1-1024x576.png)
ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሶማሊያዋ ከፊል ራስ ገዝ አስተዳደር ጁባላንድ ከፌዴራል መንግስቱ ፍላጎት ውጪ በቅርቡ ያካሔደችውን ምርጫ ተከትሎ የሞቃዲሾ መንግስት ትላንት ጥቃት መሰንዘሩን ነው መረጃዎች ያመለከቱት፡፡
በዋና ከተማዋ ሞቃዲሹ ራስ ካምቦኒ አካባቢ መነሻቸውን ያደረጉ የፌዴራል መንግስቱ ድሮኖች በጁባላንድ ኃይሎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን የግዛቲቱ ምክትል የጸጥታ ጉዳዮች ሚንስትር አዳን አህመድ ሐጂ በዋና ከተማዋ ኪስማዩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የሶማሊያ መከላከያ ሚንስትር አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር ግን የጁባ ላንድ ኃይሎች ግጭቱን እንደጀመሩት ቢያስታውቁም የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ ለቆት የወጣውን በታችኛው ጁባ የሚገኝ አካባቢ የፌዴራል መንግስቱ ኃይሎች ለመቆጣጠር በመሞከራቸው ውጊያው መጀመሩን አልሸሸጉም፡፡
ባለፈው ህዳር ወር ከአምስቱ የሶማሊያ ከፊል ራስ ገዝ አስተዳደሮች አንዷ የሆነችው ጁባ ላንድ ምርጫ ያካሔደች ሲሆን የፌደራል መንግስቱ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ በምርጫው መንግስታቸው እንዲሳተፍበት ጥሪ ሳይደረግለት በመቅረቱ እውቅና እንደማይሰጡት ገልጸው ነበር፡፡
በተፈጠረው እሰጥ-አገባም አንዳቸው በአንዳቸው ላይ የእስር ማዘዣ አውጥተዋል፤ የሞቃዲሾ መንግስት የገባበት ውጊያ አልሸባብን የመታገሉን ስራ እንዳያዳክመው ተሰግቷል ያለው የሮይተርስ ዘገባ ነው፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ