ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2017 የትምህርት ዘመን በ2ተኛ ዲግሪ /ማስተርስ ደረጃ/ ለመስጠት ያዘጋጀው የአደጋ ጊዜ ስርዓተ ትምህርት በታቀደው መሰረት መሰጠት አለመጀመሩን ነው ለመናኸሪያ ሬዲዮ ያስታወቀው፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ‘የአደጋ ጊዜ ትምህርት’ በሚል ዘርፍ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ማጠናቀቁንና በ2017 የትምህርት ዘመን በ2ተኛ ዲግሪ ደረጃ ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ ማለቱን ተከትሎ፤ አሁን ላይ እቅዱ ከምን ደረሰ? ምን ያህል ተማሪዎችንስ ተቀበላችሁ? ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ተቋሙን ጠይቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ብርሃነመስቀል ጠና፤ በዘርፉ የሚያስፈልጉ በርካታ ሙያተኞችን ለማፍራት ታስቦ ስርዓተ ትምህርቱ በባለድርሻ አካላት እና በገምጋሚዎች ማረጋገጫ ተሰጥቶት በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸውን ተማሪዎች በ2ተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅት ቢደረግም ለመማር ያመለከተ ተማሪ ማግኘት እንዳልተቻለ አስታውቀዋል፡፡
በስርዓተ ትምህርቱ በፀጥታ ችግር ምክንያት ከትምህርት የራቁ ዜጎች ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲመለሱ እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያ ሆነው ትምህርት እንዲያገኙ ታቅዶ እንደነበርም ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጅ ተቋሙ በበቂ ሁኔታ የማስተዋወቅ ስራ ባለመስራቱ ምክንያት አሁን ላይ በታቀደው መሰረት አለመጀመሩን ነው የተናገሩት።
ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ የትምህርት ዘመን በዘርፉ መማር ለሚፈልጉ እና የ2ተኛ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና (GAT) ተፈትነው ያለፉ ተማሪዎችን እንደሚቀበል አመላክተዋል፡፡
በዘርፉ ባለሙያዎችን ማፍራት የሚፈልጉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ