ኅዳር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከተመሰረተ 88 ዓመታትን ያስቆጠረው ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በ2015 ዓ.ም ጥቅምት ወር ላይ የዕድሳት መርሃ ግብሩን ካጠናቀቀ በኋላ በአዳዲስ ስራዎች እንደመጣ ሲገልጽ መቆየቱ የሚታወስ ቢሆንም በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ቲያትር ማሳየት ካቆመ ወራቶች ተቆጥረዋል፤ በዚህም ምክንያት በሙያተኞቹ ላይ ቅሬታ መፍጠሩን መናኸሪያ ሬዲዮ ለማወቅ ችሏል፡፡
ለወራት በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ቲያትር ማሳየት አቁሞ የነበረዉ ቲያትር ቤቱ አሁን ላይ ቬርሙዳ እና የደፈረሱ አይኖች፣ ነገሩ አይቆምምና ሌሎችም ትዉፊታዊ ቲያትሮችን ለተመልካቾች ሊያቀርብ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታዉቋል፡፡
የቲያትር እና ፊልም ባለሙያው ዩሐንስ አፈወርቅ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ ቲያትር ሳይታይ መቆየቱና በአካባቢዉ ያሉ ማህበረሰቦች መነሳታቸዉን ተከትሎ እንደ በፊቱ በቂ ሰዉ ላይመጣ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለዉ ገልጿል፡፡
ቲያትሮቹን ለእይታ ለማቅረብ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ያለ ሲሆን የሚቀሩና የሚሟሉ ስራዎች መኖራቸዉን ገልጾ፤ እነርሱን የማሟላት ስራ እየተሰራ እንዳለና በቀዳሚነት በቤርሙዳ ቲያትር የተቋረጠዉ የቲያትር ቤቱ ስራ እንደሚጀመር ተናግሯል፡፡
ከዚህ ቀደም የቲያትር ቤቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ በነበረዉ አርቲስት አብዱልከሪም ጀማል ምትክ በጊዜያዊነት ቦታዉ ላይ አቶ ዩሐንስ ስለሺ እንደተቀመጡ ገልጸዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ Telegram (https://t.me/menaharia_fm)
ትክክለኛውን የመናኸሪያ ሬዲዮ የዩቱዩብ አድራሻ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
➲ Youtube (https://www.youtube.com/channel/UC8uROsU69D8Ob65XapeHvIw)
ምላሽ ይስጡ